ተስፋ የቆረጠው አገዛዙ በወረታ ከተማ ተከታታይ የሆነ የሰው አልባ አውሮፕላን ድብደባ እየፈፀመ መሆኑ ተሰምቷል!

በእግረኛ ሰራዊቱ ተስፋ የቆረጠው አገዛዙ በአሁን ሰዓት በወረታ ከተማ ተከታታይ የሆነ የሰው አልባ አውሮፕላን ድብደባ እየፈፀመ መሆኑ ተሰምቷል!

በከተማዋ ከረፋድ ጀምሮ የድሮን ቅኝት እየተደረገ መሆኑን ጣቢያችን መረብ ሚዲያ ከሰዓታት በፊት ባወጣው ዘገባ መግለፁ አይዘነጋም።

አገዛዙ በከተማዋ እየፈፀመ የሚገኘው የድሮን ጥቃት የሕዝብ መገልገያ ተቋማት እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ያነጣጠረ ነው።

ፋኖ ከክልሉ ርዕሰ መዲና ባሕርዳር ከተማ በ55km ርቀት በምትገኘው ወረታ ከተማ ላይ ዛሬ የካቲት 08/2018 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ ባደረገው ከባድ ተጋድሎ የጠላት ምሽጎችን በመስበርና በርካታ የጠላት ኃይልን በመደምሰስ ከተማዋን በቁጥጥሩ ስር አስገብቷል።

ከንጋት ጀምሮ በርካታ እግረኛ ወታደሮቹ የተደመሰሱበትና ከተማዋም በፋኖ ቁጥጥር ስር የገባችበት አገዛዙ፡ ንፁኋንን እና የሕዝብ መገልገያ ተቋማትን እንዲሁም መኖሪያ ቤቶችን ያነጣጠረ የድሮን ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል።

ከፋኖ ጋር የእጅ በእጅ ውጊያ አድርጎ ማሸነፍ ያልቻለው አገዛዙ፡ ንፁኋን ላይ እና የሕዝብ መገልገያ ያተቋማት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመፈፀም፡ የፋኖ ኃይል በንፁኋን ላይ የሚፈፀመውን ጭፍጨፋ ለማስቆም ሲል ከተሞችን ለቆ እንዲወጣ ማስድረግ የሚል እቅድ ነድፎ እየሰራ ነው ሲሉ የመረብ ሚዲያ ወታደራዊ ምንጮች ገልፀዋል።