የጎንደሩ ድል የብልፅግናን አቅል አስቶታል። ሙሉ ወታደራዊ ስምሪቱ ተዛብቷል። በበርካታ ወረዳወች ላይ የሰፈረ የጠላት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል።
ተደምስሷል ማለት ተማርኮ፣ ተመቶ፣ ተበትኖ ከስምሪት ውጭ ሆኗል ማለት ነው። ድምሰሳው ሰራዊቱን ብቻ ሳይሆን ካድሬውንም ይጨምራል።
ከተበተነው የጠላት ኃይል መካከል 300 ሚሊሻ፤ 200 አድማ ብተና በድምሩ አምስት ሰራዊት እና በርካታ ቁጥር ያላቸው የመደበኛ ፖሊስ አባላት ከተለያዩ ወረዳወች በመሸሽ ባህርዳር አባይ ማዶ ሰማእታት አርፌ ነበር። የብልፅግና አመራር እና የአብይ ጀነራሎች ይህንን ኃይል በማግባባት ወደ ውጊያ ለመመለስ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም።
ወደ ቀጠናው ተመልሰን ወገናችን ጋር አንዋጋም የሚለውን አቋም አስይዛችኋል የተባሉ 135 ያህል አድማ ብተና፣ 144 ምሊሻ፣ 49 መደበኛ ፖሊስ አባላት ትጥቃቸውን አውርደው ታስረዋል።
ሌሎች ትጥቅ አናወርድም ያሉ 47 አድማ ብተና 80 ሚሊሻ ከነ ትጥቃቸው ከተማ ውስጥ ተበትነዋል። ብልፅግና ቀሪወቹን በማግባባት ላይ ተጠምዷል።
ጎንደር ላይ በገጠመው ሽንፈት ተስፋ የቆረጠው ጠላት አማራ የሆኑ የመከላከያ ሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖችን እና አባላትን እየረሸነ ይገኛል።