የእስራኤል የመብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ የአገሪቱ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ አገራቸው እንዳይመልስ ጠየቁ።

የእስራኤል የመብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ የአገሪቱ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ አገራቸው እንዳይመልስ ጠየቁ። የመብት ተሟጋች ድርጅቶቹ፣ በኢትዮጵያ ያለው የጸጥታ ሁኔታ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች እንዲመለሱ የሚያስችል አይደለም ማለታቸውን የእስራኤል ጋዜጦች ዘግበዋል።

የአገሪቱ መንግሥት በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት ለጥገኝነት ጠያቂዎች የሠጠውን ጊዜያዊ ከለላ ከዓመት በፊት ማንሳቱን ተከትሎ፣ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ውሳኔውን በመቃወም ለአገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው ነበር። ፍርድ ቤቱ ግን መንግሥት ኢትዮጵያዊያኑን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ከአገር ለማባረር ያሠለፈውን ውሳኔ እንደማያግድ መወሠኑ ይታወሳል።

የአገሪቱ ባለሥልጣናት፣ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሁኔታ ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመመለስ የሚያስችል ሁኔታ ተሻሽሏል ማለታቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሠዋል። የእስራኤል መንግሥት ኢትዮጵያዊያኑ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ የሠጠው የአራት ወራት የጊዜ ገደብ በቀጣዩ ሚያዚያ 10 ይጠናቀቃል።