ምኒልክ ዕዝ ተወርዋሪ በላጎ ሻለቃ ለወራቶች የሰለጠኑ ኮማንዶ ፋኖዎችን አስመረቁ::

ምኒልክ ዕዝ ተወርዋሪ በላጎ ሻለቃ ለወራቶች ያሰለጠኗቸውን በርካታ ምልምል ኮማንዶ ፋኖዎች ዛሬ የካቲት 5/2018 ዓ.ም በሃይማኖት አባቶችና በሃገር ሽማግሌዎች ምርቃን ታጅበው በደማቅ ሁኔታ አስመርቀዋል::
ደሴ ከተማ ዙሪያ ወረዳ እና በተለያዩ የቤተ-አማራ አካባቢዎች በርካታ ተጋድሎዎችን እያደረጉ አመርቂ ድሎችን እያስመዘገቡ ያሉት የምኒልክ ዕዝ ተወርዋሪ በላጎ ሻለቃ አናብስቶች በትጥቅና በሰው ሃይል ራሳቸውን እያጠናከሩና እያደራጁ ይገኛሉ:: በቀጣይም ተጨማሪ ስልጠናዎችን በማካሄድ በእውቀትና በሰው ሃይል እንዲሁም በትጥቅ የበለጠ ራሳቸውን እንደሚያደራጁ የተወርዋሪ ሻለቃዋ አመራሮች ገልፀዋል::
ከዚህ ጋር ተያይዞም አባቶች በተገኙበት ለወራቶች የሰለጠኑ ምልምል ኮማንዶ ፋኖዎችን በማስመረቅ የሰው ሃይላቸውን ያጠናከሩ ሲሆን በምርቃን ዝግጅቱ ላይ የተገኙ አባቶችም የአማራ ህዝብ የብዙ እሴቶች ባለቤት ነው እናንተ ልጆቻችንም ይሄንን እሴታችንን ተላብሳችሁ የህልውና ትግሉን ከዛሬ አድርሳችኋል ወደፊትም ይህንን ጠብቃችሁ ለድልና ነፃነት እንድታበቁን አደራ ጥለንባችኋል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል::
ሰልጥነን እንዋጋለን፣ እየተዋጋን እንሰለጥናለን!
©በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!