መተዛዘቢያ ስለ አባ ሠረቀብርሃን ወልደ ሣሙኤል

መተዛዘቢያ ስለ አባ ሠረቀብርሃን ወልደ ሣሙኤል

በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቀሲስ አስተርአየ የነነዌ ጾም ከኢትዮጵያውያ ጋራ ያላትን ንክኪ ገልጸው በማቅረባቸው ብዙውን ሰው አነጋግሮታል፡፡

ምእመኑ የተነጋገረበትን ያህል ጳጳሳቱ ቀሳውስቱና ዩቱብ ከፍተው ስለ ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ ነገር ብቅ እያደረጉ የሚናገሩት ዩቱበሮች የተነጋገሩበት አይመስልም፡፡

ለምንድነው ያልተነጋገሩበት ? የሚል ጥያቄ ተነስቶ ቀሲስ የሚናገሩት ከተራ ካዴሬና ከመንደርተኛ ወሬ የራቀ በቤተ ክርስቲያኗ ቋንቋ ነው። ዩቱበሮቹ ግን በቤተ ክርስቲያኒቱ ትምህርት የገቡ አይደሉም፡፡ ከማንኛውም ሰው የተለዩ አይደሉም፡፡ ቀኖናውንም ነገረ መለኮቱንም አይረዱትም፡፡ ቅኔውም ይከብዳቸዋል፡፡ እንደ ቀሲስ ከግል ወዳጅነትና ከግል ጥቅም የራቁ አይደሉም፡፡ ቀሲስ ለማሳየት የሚጥሩት ጥንታዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ብጹአንና ቅዱሳን ከሚባሉት በተለያዩ አጽያፊ ተግባሮች በሚከሰሱት በሚወቀሰቱና ከትዝብት ላይ በወደቁት ጳጳሳት ልክ እንዳትለካ ብቻ ነው፡፡ እየተከፋፈሉ እርስ በርሳቸው ከሚደባደቡትን ጳጳሳት ካንዳቸውም ግላዊ ወዳጅነትም ሆነ ውለታ የላቸውም፡፡ አድርባነትም የሚያጠቃቸው አይደሉም፡፡

እንደ ሌሎቹ በወዳጅነት፣ በዘረኝነትና ጎጠኝነት እንዲሁም በአምቻ ጋብቻና በጓደኝነት በጥቅም ወይም ቅስናውን ስለሰጧቸው ውለታ የመክፈል ግዴታ የለባቸውም፡፡ ሌሎቹ ቄሶች ቆሞሶችና ሰባኪወች ለቀኖናው ለነገረ መለኮቱ ለጠቅላላዋ ቤተ ክርስቲያን ሳይጠነቀቁ በተሳሳተ መንገድ ወደ ሲኖዶሱ ለገቡት ጳጳሳት እንጠንቀቅ እያሉ ይሰብካሉ፡፡ ለምን ጵጵስና ተተቼ ብለው ለቤተ ክርስቲያን ክብር የቆሙ መስለው ሕዝቡን ያደናብሩታል፡፡ ቀሲስ አስተራየን ከሌላው ልዩ የሚያደርጓቸው ከማንም ግለ ሰብ ጋራ ሳይወግኑና ወገነተኛ ሳይሆኑ የተሳሳተመስሎ የታያቸውን ሳይመክሩና ስይገስጹ አለማለፋቸው ነው፡፡

ከ2 አመታት በፊት አባ ሠረቀ የተባሉት  “ሠረቀ” እንደ ግዕዙ ሳታላሉ እንደ አማርኛው ጠበቅ አድርጉትና ሰረቀ፣ ዘረፈ፣ ነጠቀ ብላችሁ አንብቡት።  እኝህ ሰው “ኢትዮጵያን ትፏት” ሲሉ የተናገሩትን ሰምተው ከነነዌ ጾም በኋላ በድሮ ቅኔ የታጀበች ጦማር ጽፈውላቸው ነበር፡፡ የቅኔው ይዘት ለተራው ሰው ለመረዳት አስቸጋሪ ቢሆንም ጽሁፏ ራሳቸው አባ ሠረቀ በተናገሩት እንዲጸጸቱና ንስሀ ገብተው ከቂም ከበቀል ከቁጣ ወጥተው የቆሰለው እንዲፈወስ፣ የተሰበረው እንዲጠገን፣ የፈረሰው እንዲገነባ ተባብረን እንቁም የሚል ነበር፡፡

አባ ሠረቀ የቀሲስን ምክር በመስማት ለኢትዮጵያ ለቤተ ክርስቲያንና ለራሳቸው ህዝብም አልቆሙም፡፡ ከዚያ ወዲህ በተሳሳተ መንገድ ቀኖናውን ሰብረው ያለ ፓትርያርኩ ቡራኬ ራሳቸውን ጵጵስና ሰይሙ፡፡ ሰውየው በህወሃቱ ደብረ ፅዮን ጵጵስና የተሰጣቸው መሆኑንን ቢኩራሩበትም ያልገባቸው ነገር “በፋሲካ የተቀጠረች ገረድ ሁል ጊዜ ፋሲካ ይመስላታል” እንደሚባለው አሁንም ህወሃት ስልጣን ያለውና ፈላጭ ቆራጭ ይመስላቸዋል። ሰውየው የብዙ ሰው ደም እጃቸው ላይ ስላለ በቁማቸው ያራዣቸዋል። ህወሃት አሁን በአብይ አህመድ መልካም ፈቃድ ቀለብ የሚሰፈርለት፣ ነዳጅ የሚቀዳለትና ወደ ውጭ አገር ለመሄድ ይለፍ የሚሰጠው ደካማ፣ በአውራጃና በመንደር የተከፋፈለ ልፍስፍስ ድርጅት መሆኑን አይታያቸውም። እሳቸውንም ከአውስትራሊያ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ከልክሎ ኤርፖርት ላይ እንኳን መጸዳጃ ቤት እንዳይጠቀሙ አስፈራርቶ ወደ መጡበት እንደላካቸው ይረሳሉ። አሁንም ጥላቻቸውና ጥርሳቸውን የሚያፋጩት ጀኖሳይድና የዘር ማጥፋት የሚፈጸምበት ምስኪሉ የአማራ ህዝብ ላይ ነው። አባ ሰረቀ የቆሞሥነቱን ቆብ አውልቀው፡ የጵጵስና ቆብ ደፍተው ጢማቸውን ከፍክፈው የጳጳስ ዱሉ ተሽክመው ወደ ፊት በመምጣት የትግራይን ቤተ ክርስቲያን ከፈሏት፡፡ አሁን ከነ ሳዊሮስ ጋራ በደላላዋ እጅጋየሁ በየነ አቃጣሪነት እየተንፏንቀቁ የተፏትን ኢትዮጵያ ሊልሷትና ሊውጣት በዓቢይና ጌታቸው ረዳ በኩል ወደ ዋናው ቤተ ክህነት ለመግባት እንደ እባብ በደረታቸው በመሳብ ላይ ናቸው፡፡

ከሁለት አመት በፊት ቀሲስ አስተርአየ ለአባ ሠረቀ የጻፉላቸውን ጦማር ከዚህ በታች አንብባችሁ የራሳችሁን ትዝብት ውሰዱ። ለቆሞስ አባ ሠረቀ ከቀሲስ አስተርአየ ጽጌ