የነነዌ ጾም ዕንድምታና የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች
በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
“በመሸ ጊዜ ሰማይ ቀልቷልና ብራ ይሆናል ትላላችሁ፡፡ ማለዳም ሰማይ ደምኖ ከብዷልና ይዘንባል ትላላችሁ የሰማዩን ፊትማ መለየት ትችላላችሁ፡፡ የዘመኑን ምልክት መለየት አትችሉም፡፡ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፡፡ ከነቢዩ ከዮናስ በቀር ምልክት አይሰጠውም”(ማቴ 16፡3-4)፡፡
ዘመን ተተካኪው ትውልድ በእምነት በታሪክ በባህል ተሳስሮ የሚሸጋገርበት ድልድይ ነው፡፡ በዘመን ድልድይነት እየተተካ የሚቀጥለውን ትውልድ ሀዘንም ደስታም ይገጥመዋል፡፡ የሚገጥመውን ሀዘንም ሆነ ደስታ የሚገመግምበት የሚገምትበትና የሚተረጉምበት ምልክት አለው፡፡ ምልክቱም እየተተካካ የመጣው የቀደመው ትውልድ ለረዥም ዘመን ያጠራቀማቸው ተግዳሮቶች የተሻገረባቸው ጥበቦች ፈሊጦችና ማስተዋሎች ናቸው፡፡
እየተተካካ የመጣው የቀደመው ትውልድ ለረዥም ዘመን ያጠራቀማቸው ተግዳሮቶች የተሻገረባቸው ጥበቦች ፈሊጦችና ማስተዋሎችን እንደ መረጃ ምልክቶች አድርጎ ከገጠመው መከራ አሸንፎ ለመውጣት ከተሳነው፡፡ ከሚገጥመው መከራ ካባቶች የወረሰውን ዘዴ መጠቀም አቅቶት በሌላ አዲስ ጠቋሚ ምልክት አሸንፎ ከገባበት መከራ ለመውጣት እድል የለውም፡፡ እንደ ነቢዩ ዳዊት በራሱ ትጥቅ (ወንጭፍ)ከመታገል ይልቅ ትጥቁን ፈቶ በሌላ ትጥቅ ለመፋለም መሞከር ለድል አያበቃም፡፡
“ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፡፡ ከነቢዩ ከዮናስ በቀር ምልክት አይሰጠውም” እንዳለው ሻብያና ወያኔ ተወዳጅተው ኢትዮጵያን ወግተው ኢትዮጵያን በዘር በጎሳ በቋንቋ በታትነውና አጣልተው፡፡ ለዘላለም ለዘላለም እየበዘበዙ ለመኖር የአማራውን ስነ ልቡና ስብረው፡፡ የቀረው ዜጋ ሁሉ በአማራው ላይ እንዲዘምትበት አድርገው ለ7 አመት ሲበዘብዙ ከኖሩ በኋላ የኃጢአታቸው ጽዋ ሞላ፡፡ አማራውን ሲአፋጁ በኖሩት በሁለቱ ወዳጆች ማለትም በኢሳይያስና በመለሰ መካከል ጠላትነት ፈነዳ፡፡ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያን ማፋጀታቸው ቢያስዝንም፦መልካምነቱ በኢትዮጵያ ደም ኤርትራን ሲንጋፖር ለማድረግ የኢስይያስ እቅዱ ከሸፈበት፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዓቢይ ወደ ሥልጣን እስኪመጣ ድረስ በወያኔና በሻብያ የነበረው ጥላቻ የተዳፈን እሳተ ገሞራ ሆኖ ቆየ፡፡ ዐቢይና ኢሳይያስ አዲስ ፍቅረኞች ሆኑ፡፡ በዓቢያና በኢሳይያስ የውሸት እርቅ የተዳፈነው እልቂት ያልተከሰተለት ሞኙ ሕዝብ ደስ አለው፡፡ አጨበጨበ፡፡ ዓቢይ ከወያኔ ተፋታ ከሻብያ ጋራ ተጣመረና ጦርነት ፈነዳ፡፡ በቀደመ ወዳጁ ካደኝ በሚለው በሻብያና በቅርብ ወዳጁ በዐቢይ ሕብረት ወያኔ ተደበደበ፡፡
አሁን ደግም በዚህ ዐመት በነደብረ ጽዮን የሚመራው ወያኔ ከወዳጁ ከዓቢይ ጋራ የነበረውን የፍቅር ጥምረት በጥሶ ከቀደመው ጠላቱ ከሻብያ ጋራ አጣምሮ የሁለቱን ወዳጅና ጠላት እየሆነ የቀጠለውን የዓቢይን መንግሥት ለመውጋት እየፎከረ ነው፡፡ በዚህ ምስቅልቅል የሚያልቀውን ወጣት የኤርትራ የትግራይና የኢትዮጵያ ጳጳሳት አንድ ላይ ቆሞው፡ ለኤርትራና ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰሎሞንና የክርስቶስን ጥበብ በመከተል ከንግሥተ አዜብ እና ከነነዌ ሰወች ፍርድ አምልጡ! በደም ተንክረው አቅጣጫ በመቀያየር እርስ በርስ የሚያፋጇችሁን የእልቂት መሪወችን ዮናስ ከመርከባቸው አውጥተው እንደጣሉት ከተቀመጡበት ወንበር እይፈነገላችሁ ከመካከላችሁ አውጥታችሁ ጣሏቸው! ማለት ይገባቸው ነበር፡፡ ከዚህ በቀር ለጳጳሳት ለህዝቡ ሌላ አማራጭ ምልክት አይሰጠውም፡፡
ቪዲዮውን ለመከታተል እዚህ ላይ ይጫኑ።

ከላይ የሰፈረውን ሀሳብ በመተንተን ቀሲስ አስተርአየ “ከፍኖተ ርዕይ” ጋር ያደረጉትን ውይይት ይከታተሉ።