“አብይ አሕመድ እስር ቤት” የሚገኙ እስረኞች ኢሰብአዊ አያይዝን በመቃወም አድማ ላይ ናቸው

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ሥር በአባ ሳሙኤል አካባቢ በሚገኘው አብይ አሕመድ እስር ቤት የሚገኙ እስረኞች እየተፈጸመብን ነው ባሉት ኢሰብዓዊ አያያዝ ምክንያት ካለፈው ሰኞ ጀምሮ የረሃብ አድማ ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ማረሚያ ቤቱ፣ የውሃ፣ ምግብ፣ መጸዳጃ ቤት፣ መኝታና የምግብ ማብሰያ ቦታ ችግሮች እንዳሉበት ታውቋል።

እስረኞቹ ቅሬታቸውን በተወካዮቻቸው በኩል አቅርበው እንደነበርና ኾኖም ምላሽ ባለማግኘታቸው የርሃብ አድማ ለመምታት እንደተገደዱ ምንጮች ገልጸዋል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ከቀናት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ፣ የእስረኞች የቀለብ ማስተካከያ ጥያቄ መልስ ባለማግኘቱ አንደንድ ታራሚዎች ግርግር ለማስነሳት እየሞከሩ እንደኾነ ተናግሮ ነበር።