የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ በተሳተፉበት ውይይት ለዓመታት በታጣቂወች ታግተው የነበሩ ሴቶችን ማስለቀቅ ተችሏል።
በመተከል ቀጠና በለተያዬ ጊዜ በነበሩ አገዛዙ በፈጠራቸው ግጭቶች ምክንያት በርካታ አማራወች ሲፈናቀሉ፣ ሲጨፈጨፉ እና ሲታገቱ የቆዩ መሆኑ ይታወቃል። ሊቀመንበሩ በቀጠናው ካሉ ታጣቂወች ጋር ባደረጉት ውይይት በባለፉት ዓመታት በተከታታይ በተከሰቱ በእነዚህ ግጭቶች አጋጣሚ እስከ አራት ዓመታት ድረስ ታግተው የቆዩ አስር ያህክል ሴት ወጣቶችን ለማስለቀቅ ተችሏል።
በቀጠናው ከሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ኃይሎች ጋር ቀናትን የወሰደ ውይይት ያደረጉት አርበኛ ዘመነ ካሴ እህቶቻችንን ከታገቱበት ቦታ ተረክበው ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ሸኝተዋቸዋል።
በእለቱም አርበኛ ዘመነ ካሴ ተከታዩን መልዕክት አስተላፈዋል።
“እኛ አማራዎች ሰው ከሚፈጥረው የፖለቲካ ክፋትና ፀረ አማራ ርእዮት ጋር እንጅ ከሰው ልጆች ጋር ፀብ የለንም።ሰው ክቡር ነው። ርእዮታችን የሚቀዳውም ከዚህ የአስተሳሰብ ባህር ነው።እና ማንም ህዝብ ወገናችን ነው። (በዚህ ጉዳይ የጉምዝ ህዝብም)። ስለዚህ በመተከል በጉምዝና የአማራ ህዝብ መካከል፥ በሽናሻና የአማራ ህዝብ መካከል፥ በቤኒሻንጉልና የአማራ ህዝብ መካከል መገዳደልን ሊዘራ የሚሞክረውን የረጅም ጊዜ የጠላት አስተሳሰብ እየነቀልነው በቦታው ፍቅርንና አብሮነትን እየተከልን ነው።በዚህም የተነሳ ከድርጅቶች ጋር ጥሩ መቀራረብ ፈጥረናል።
በመሆኑም በተለያዬ ጊዜ በተነሱ ግጭቶች ምክንያት በጉምዝ ሃይሎች ከስራ ቦታቸው እየተያዙ እስከ አራት አመታት ታግተው የቆዩ አስር የአማራ ልጆችን ማስመለስ ችለናል። በዚህ ወቅት እህቶቻችን ተረክበን ወደ ቤተሰቦቻቸው እየላክን እንገኛለን።ይቀጥላል።”
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተለያዬ ማንነት ካላቸው ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን የአጋርነት እና የትብብር ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በዚህ ረገድ ድርጅታችን በኢትዮጵያ ህልውና፣ በህዝቦች አብሮነት፣ እና በአገዛዙ የጋራ ጠላትነት ላይ የተመሰረቱ ተጨባጭ ስራወችን አጠናክሮ የሚሰራ ይሆናል።
የአማራ ህዝብ የሰላም፣ የአንድነት፣ የአብሮነት እሴቶችን በሚያጎለብት መንገድ በሁሉም ማዕዘናት ለሚኖረው ህዝባችን ደህንነት አስፈላጊዉን ሁሉ ማድረጋችን ይቀጥላል።