ከላላ ወረዳ ቲርቲራና ሻፊ ላይ በተደረገ ተጋድሎ ፋኖ ታላቅ ድል ተቀዳጀ!
በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር አርበኛ አደም አሊ (አባ ናደው) ክፍለ ጦር ከላላ ወረዳ ቲርቲራና ሻፊ ከተማ ላይ ጥር 26/2018 ዓ.ም ከፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ሰራዊት ጋር ብርቱ ትንቅንቅና ተጋድሎ በማድረግ ከሃያ በላይ በመደምሰስና ከሃያ ያላነሰ በማቁሰል ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል ተጎናፅፈዋል::
ተከጋድሎው ከቲርቲራና ሻፊ ከተማ ባሻገር ልዩ ስሙ ቡሶ የተባለ አካባቢ ላይ ከብልፅግና መከላከያ ሰራዊት ውጭ በርካታ አድማ ብተናና ሚሊሻ በአባ ናደው ልጆች አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ለባንዳ የሚገባውን ሰጥተዋል::
ባጠቃላይ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር ውግዲ ዙሪያ እና ቲርቲራና ሻፊ ከተሞች ጠላትን ከባድ ምት በመምታትና በርካታ ቁስለኛ ወደ ወግዲ ሆስፒታልና ደሴ ሆስፒታል እንዲያግዝ በማድረግ ብሎም የዘመቻ እቅዱንም ባጭር በማስቀረትና በማክሸፍ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ!