ንጉስ ሚካኤል ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ወግዲ ወረዳ ዙሪያ ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::
እንደሚታወቀው ፀረ አማራው ብልፅግና በሰሜን ወሎ እና ደቡብ ወሎ በደረሰበት ሽንፈት ወደ ደቡብ ወሎ ቀጠና እና አጎራባች ሸዋ ለመስፈር አሰቦ መካናይዝዱን ሳይቀር ሙሉ ጦሩን እያሽሽ እና እያንቀሳቀሰ ይገኛል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም በዛሬው ዕለት ሙሉ ሀይሉን ሰብሰቦ በወግዲ ወረዳ አድርጎ ወደ ሸዋ ለመውጣት የሞት ሽረት ከባድ ትንቅንቅ ለማድረግ ቢሞክርም መብረቆቹ የሚቀያይረውን ሀይል ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ በመምታት ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::
ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ጠላት ሰብሮ ሊወጣ የነበረበትን ስትራቴጅካዊ ቦታ በወግዲ ወረዳ ጎርንጅ ቀጠና ከሌሊት 11፡00 ሰዓት ጀምሮ በደፈጣና እና በፊት ለፊት ውጊያ ሙትና ቁስለኛ አድርገውታል። በነበረውም ተጋድሎ ጠላትን ምድር ገበያ ላይ የገባው ሀይል በደፈጣ ሙሉ በሙሉ ሲደመሰስ መልሶ ቢደራጀም በድጋሜ ኢላላ እና አጋምሳ ከተባለ ቦታ ላይ በተሰነዘረ የፊት ለፊት ማጥቃት የብልፅግናው ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ካሰበበት ቦታ ሳይደረስ ወደ ኋላ በከባድ ኪሳራ ለመመለስ ተችሏል ። በተደረገውም ተጋድሎ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጠላት ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ወደመጣበት ተመልሷል::
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ!