በብልፅግናው አገዛዝ አጋቾች ታግተው የነበሩ ሰባት የኦሮሞ ተወላጆች በፋኖ ነፃ ወጡ!

በብልፅግናው አገዛዝ አጋቾች ታግተው የነበሩ ሰባት የኦሮሞ ተወላጆች በፋኖ ነፃ ወጡ!

ታጣቂዎችን በመመልመልና በማደራጀት አሰማርቶ ንፁኋንን በማሳገት ገንዘብ የሚሰበስበው የብልፅግና ቡድን፡ በደራ ቀጠና አሰማርቷቸው በነበሩ አጋቾች ታግተው የነበሩ የኦሮሞ ተወላጆች የሆኑ ሰባት ንፁኋኖች ፋኖ ባካሄደው ብርቱ ውጊያ ነፃ መውጣታቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

ብልፅግና “ነፍጠኛ ሊጨፈጭፋችሁ እየመጣነው ተነሱ ታጠቁና ዝመቱ” በሚል በኦሮሚያ ክልል ወታደራዊ ምልመላ እያካሄደ ባለበት ወቅት ፋኖ በብልፅግና አጋቾች የታገቱ ኦሮሞዎችን ነፃ ማውጣቱ ብዙዎችን አነጋግሯል።

ይህም ትክክለኛውን የፋኖን የትግል መስመር ፍንትው አድርጎ ያሳየ ነው ተብሏል።