በአገዛዙ ታፍነው ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ጣቢያ ተወስደው የነበሩ ምልምል ሰልጣኞች ከማሰልጠኛ ጣቢያው ጠፍተው ፋኖን ተቀላቀሉ!!
የፋሽስቱ ዐብይ አህመድ አገዛዝ ስልጣኑን በታዳጊዎች ደምና ጉልበት ለማቆዬት ከተለያዬ የመዝናኛ ቦታ እንዲሁም ከትምህርት ቤት አፋኖ ወደ ብርሸለቆ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም አስገብቷቸው የነበሩ ምልምል ሰልጣኞች “ሰልጥነን ወጥተን በአማራ ሕዝብ ላይ ጭፍጨፋ አንፈፅምም” በሚል በመጥፋት አፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ 109ኛ ኮር 77ኛ ክ/ጦርን መቀላቀላቸውን የኮሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
አገዛዙ በኃይል አግቶ ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ካስገባቸው በኃላ ከከዳችሁ ፋኖ ያርዳችኋል፣ይቆራርጣችኋል እያለ የማስፈራሪያ ፕሮፖጋንዳ እንደ እንደሚነገራቸው ሰልጣኞች አክለው አስረድተዋል።
ዳሩ ግን ቴዎድሮስ ዕዝ የ109ኛ ኮር ከዚህ ቀደም ከተለያዬ የሀገሪቱ ክፍሎች ታፍነው የሚመጡ ሰልጣኞችን ልዩ እንክብካቤ በማድረግ የትራንስፖርት ወጭያቸውን በመሸፈን ከ136(አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት) በላይ ምልምል ሰልጣኞችን ወደ ትውልድ ቀያቸው በክብር በመሸኘት እና ከወላጆቻቸው ጋር በማገናኘት የወገን አለኝታ መሆኑን በተግባር አስመስክሯል።
ወደ ማሰልጠኛ ታግተው የገቡት ኢትዮጵያውያን ዕድሜያቸው ከ15-17 የዕድሜ ክልል እንደሚገኙ ምልምል ሰልጣኞች ለፋኖ አስረድተዋል።