አማራ ጠሉ የአብይ አህመድ ስርዓት ገበያ በወጣ ህዝብ ላይ ግፍ ፈፀመ።
በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን መቄት ወረዳ ፍላቂት ትላልቅ ፎቆችን እንደ ቤተ መንግስት አስቦ የሚኖረው የአፓርታይዱ አብይ አህመድ ስርዓት ያለ የለለ ኃይሉን አንቀሳቅሶ መቄት ወረዳ አግሪት ገበያ በወጡ ንፁሃን ላይ የጥላቻ በትሩን አሳርፎ ወደ መደበኛ ጉሬው ፍላቂት ፎቅ ስር ተመልሶ ተወሽቋል።
መቄት ወረዳ አግሪት ገበያ ላይ ከ100 በላይ ወጣቶችን አፍሶ የተመለሰው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ንፁሃን ላይ ከፍተኛ ድብደባ፣እንግልትና ወከባ በማድረስ የበቀል በትሩን አሳርፏል።
የገበያ ቀንን እና እለተ ሰንበትን ጠብቆ የሚንቀሳቀሰው የአማራ ጠሉ አገዛዝ ሰራዊት ፋኖን በአውደ ውጊያ ከመፋለም ይልቅ ህዝብን ማሸበር እና ማንገላታትን ዋነኛ የውጊያ ስልት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ በአደባባይ ያረጋገጠ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ገልፀዋል።
የዛሬውን አግሪት ገበያ ወጣቶችን አፈሳ እና ለገበያ የወጣውን ንፁሃን ህዝብ ድብደባና እንግልት ያስተባበረው ጥቁር አማራ የመቄት ተወላጁ ኢንስፔክተር አየሁ በላይ እንደሆነ የመረጃ ምንጮቻችን ያመለክታሉ።
©በአፋብን ምኒልክ ዕዝ ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ!