በሰሜን አማራ ቀጠና ወርቅ ደቦ ከተማ በተደረገ ውጊያ ከ15 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ!

በሰሜን አማራ ቀጠና ወርቅ ደቦ ከተማ በተደረገ ውጊያ ከ15 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ተደረጉ!

በከተማዋ አገዛዙ ጥምር ኃይል ብሎ የሚጠራቸው የመከላከያ ሰራዊት፡ የአድማ ብተናና የሚኒሻ ኃይሎች በጋራ በመሆን ጥቃቱን ለመከላከል የሞከሩ ቢሆንም ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተሰነዘረባቸውን የፀረ መከላከልና የመልሶ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም አቅቷቸው ከባድ የሰብአዊና ቁሣዊ ኪሳራ መከናነባቸውን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር  ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር ስር የሚገኙት የአጥናፋ ብርጌድ ፋኖዎች ጥር 22/2018 ዓ/ም  ከእኩለ ቀን በኋላ እስከ ምሽት ባደረጉት ተጋድሎ የጠላትን ጥምር ጦር አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ታላድ ድል መቀዳጀታቸው ታውቋል።

ውጊያው የተካሄደው በቀጠናው ወርቅ ደቦ ከተማ ውስጥ ሲሆን፡ በዚህም ፋኖ ወደ ጠላት ምሽግ ተወርውሮ በመግባት የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ አድርጎ ምሽጋቸውን ማውደሙን ነው መረብ ሚዲያ ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ የቻለው።

በዚህ ውጊያ ከ15 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሲደረጉ በርካታ የጦር መሣሪያዎችና ሌሎች ወታደራዊ ግብአቶች በፋኖ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከተገደሉ የጠላት ጥምር ጦር አባላት መካከል በቀጠናው ለጠላት ወታደሮች መንገድ በመምራትና፡ የፋኖ ደጋፊ ናቸው በሚል ንፁኋኖችን ሲያስገድልና ሲያሳስር የነበረው ቻሌ ገብሬ የተባለው የሚኒሻ አባል እንደሚገኝበት ነው መረብ ሚዲያ ከጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ለማረጋገጥ የቻለው።

በውጊያው ፋኖ፡ ከወደ ጠላት የገጠመው መከላከልን የፀረ መከላከል እርምጃ በመውሰድ የጠላትን ምሽግ ድርምስምሱን ያወጣበት ሁኔታ የማጥቃት አቅሙ ምን ያህል  እንዳለ ያሳየ ነው የተባለ ሲሆን፡ በአንፃሩ ደግሞ የአገዛዙ ኃይል ከወደ ፋኖ የተከፈተበትን ማጥቃትን ተከላክሎ ካምፑን መታደግና እራሱን ማዳን አለመቻሉ በምን ያህል መልኩ ደካማ እንደሆነ ያሳየበት ነው ብለዋል የውጊያ ተንታኞች።