ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር ተንታ እና መቅደላ ወረዳ በመቶ የሚቆጠር የብልፅግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም ሁለት የቡድን መሳሪያ እና ከ37 በላይ ክላሽ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፀፉ::

በመድፍ፣ በቢ ኤም 107፣ ዙ23 እና ሞርተሮች ታግዞ ከባድ ውጊያ የከፈተው ፋሽስቱ የብልፅግና አገዛዝ ዛሬ ጥር 22/2018 ዓ.ም ደቡብ ወሎ ዞን ተንታ እና መቅደላ ወረዳ እንዲሁም ማሻ ከተማ ዙሪያ ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ያስተናገደ ሲሆን ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር የንጉስ ሚካኤል ኮር አሃድ ከሆነው ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ጋር በመጣመር በመቶ የሚቆጠር የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ እንዲሁም በርካታ ጦር መሳሪያና ተተኳሽ በመማረክ ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

ምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር በተጋድሎው ማሻ ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በርካታ ጥምር ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ከመደምሰስ ባሻገር አንድ ስናይፐር፣ አንድ ብሬን፣ 21 ክላሽ፣ እና የእጅ ቦምቦች እንዲሁም 3000 የክላሽ ተተኳሽ ማርከዋል:: በተጨማሪም ሸህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ማሻ ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት ባንዳን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣትና በመማረክ ጭምር ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

ልጅ እያሱ ኮር 23ኛ ክፍለ ጦር ለሌላ ተጨማሪ ጦርነት እየተዘጋጀ ላለው ፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ራስ ምታት የሆነ ታላቅ ድል ማሻ ከተማ ላይ ያስመዘገቡ ሲሆን በርካታ እግረኛ ሰራዊቱ የተመታበት ብሎም የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ እንዲሁም ተተኳሽ የተማረከው አገዛዙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብቷል::
ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ያስተናገደውና የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የብልፅግና ሰራዊት የበቀል አፈሙዙን ወደ ንፁሃን ጦር መሳርያ ያልታጠቁ አማራዎች በማዞር ተንታ አካባቢ አንዲት እናት በሞርተር የገደለ ሲሆን በዙ23 ዘጠኝ መኖሪያ ቤቶችን አቃጥሏል::

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!
ህልዉናችን በተባበረ ክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ
ጥር 22/2018 ዓ.ም