የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በመቄትና ቋና በሁለት ግንባር በጥላት ሰራዊት ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::

የደጋው መብረቅ ኮር አሃዶች በመቄትና ቋና በሁለት ግንባር በጥላት ሰራዊት ላይ መጠነ ሰፊ ማጥቃት በማድረግ ታላቅ ድል አስመዘገቡ::

የደጋው መብረቅ ኮር አሀድ የሆኑት አንሻ ክፍለ ጦርና ቀኝአዝማች ተበጀ ወርቁ ክፍለ ጦር በሁለቱ ግባሮች ላይ በርካታ የብርሀኑ ጁላን መከላከያ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ተደርገዋል!

አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር አሀዶች ጥር 20/2018 ዓ/ም በሁለት ግባር  ከሶስት ወረዳዎች  ለከበባ በመጣ የብርሀኑ ጁላ መከላከያ ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት ተፈፅሟል።

ከመቄት፣ከጋሸናና ከኮን በሶስት አቅጣጫ ለከበባ የመጣው የጥላት ሰራዊት የከበባ ጥቃት የከፈተ ቢሆንም  ፤በፋኖዎቹ በተወሰደ አፀፋዊ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በሁለቱም ግባር ከ15 በላይ  የጥላት ሰራዊት ሲደመሰሱ፤ዘጠኙ  ከባድ ቁስለኛ ተደርገዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከባድ የሰብአዊና ቁሳዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራ የተከናነበው የጥላት ሰራዊት ወደመጣበት ሲመለስ በንፁኋኖች ላይ የፈሪ በትሩን አሳርፎ አርሶ አደሮችን በገፍ ጨፍጭፏል። በፋኖዎቹ የመልሶ ማጥቃት ጥቃት ክፉኛ የተከፈተበት የፋሽስቱ ሰራዊት እግሬ አውጭኝ በማለት ወደየመጣበት ምሽጉ ተመልሷል።

©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የደጋው መብረቅ ኮር  ሕዝብ ግንኙነት ክፍል