ብልፅግና የመጨረሻ ያለውን ካርዱን ወልቃይት ላይ መዟል!

ብልፅግና የመጨረሻ ያለውን ካርዱን ወልቃይት ላይ መዟል!

በጠለምት ዋልድባ አካባቢ ማይ-ዳጉሻን ጨምሮ በአራት ግንባር ከትናንት ጥር 18/2018 ዓ/ም ጀምሮ ውጊያ ተቀስቅሷል።

ብልፅግና፡ በባለቤቱ በአማራ ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ወልቃይትን ከሕወሓት ታጣቂዎች የሚከላከል መስሎ ተኩስ ከጀመረ በኋላ፡ እንደለመደው በማፈግፈግ ወልቃይትን ሙሉ ለሙሉ በሕወሓት ታጣቂዎች የማስወረር እቅድ እንዳለው ነው የተነገረው።

ስልታዊ ማፈግፈግ በሚል የአማራ ሕዝብ ላይ የነበረውን የጥላቻ ጥማት የተወጣው ብልፅግና ዛሬም በዚችው ማሊያ ለመጫዎት ካርዱን መምዘዙ ታውቋል።

አስወረርከን የሚል ጥያቄ ሲነሳበትም “የሕወሓት ታጣቂዎችን ከወልቃይት እንዳላስወጣ ፋኖ እንቅፋት ሆኖብኛል” የሚል ካርድ ለመምዘዝ መዘጋጀቱን የመረብ ሚዲያ ምንጮች ገልፀዋል።

ይህ ነውረኛና ፀረ አማራ ቡድን በአክቲቪስቶቹ በኩል የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ወልቃይትን በሕወሓት አስወረረብን የሚል የለቅሶ ፖለቲካ ለመስራት ድንኳን ተከላ ጀምሯል።