በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በተከሰተው እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ያለበት የአየር ሁኔታ ምክንያት በተለያዩ ቦታዎች የሰዎች ሕይወት እየጠፋ ነው ተባለ።

በበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ በተከሰተው እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ያለበት የአየር ሁኔታ ምክንያት በተለያዩ ቦታዎች የሰዎች ሕይወት እየጠፋ ነው ተባለ።

ካለፈው ሳምንት ማብቂያ ቀናት አንስቶ በአሜሪካ ባጋጠመው የበረዶ ወጀብ ምንም እንኳን የአንዳንዶቹን ምክንያት በትክክል ለማረጋገጥ ገና ቢሆንም እስካሁን ቢያንስ 14 ሰዎች በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ሞተዋል።

➡️ የቴኒሲ ግዛት ባለሥልጣናት ከአየር ሁኔታው ጋር በተያያዘ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጠዋል።

➡️ ከበረዶው ወጀብ ጋር በተያያዘ የሁለት ሰዎች ሞት በሉዊዚያና ግዛት ውስጥ ተመዝግቧል።

➡️ ቴክሳስ ውስጥ በአንድ ነዳጅ ማደያ ውስጥ ሞቶ የተገኘ ግለሰብ ምክንያቱ የጤና ወይም ከቅዝቃዜው ጋር የተገናኘ ሊሆን እንደሚችል ፖሊስ ገልጿል።

➡️ ቴክሳስ ውስጥ አንዲት የ16 ዓመት ታዳጊ በረዶ ላይ ስትንሸራተት በገጠማት አደጋ ሕይወቷ አልፏል።

➡️ ማሳቹሴትስ ውስጥ አንዲት ሴት በረዶ ተደርምሶባት ሞታለች።

➡️ ካንሳስ ውስጥ ደግሞ አንዲት ሴት በበረዶ ተሸፍና ሞታ ተገኝታለች።

የሞታቸው ምክንያት ገና ባይረጋገጥም ኒው ዮርክ ውስጥም አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በሌላ በኩል አሜሪካንን በመታት በሰሞነኛው ከባድ በረዶ በሜይን ዝጋት ስምንት ሰዎችን ያሳፈረ የግል ጄት ባንጎር ከተባለ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲነሳ ተከስክሷል። የተሳፋሪዎቹ ሁኔታ እና ማንነት ለጊዜ አልታወቀም።

በአሜሪካ ያለው ሁኔታ ለአየር ትራንስፖርትም ፈተና ሆኗል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ ሌሎችም አየር መንገዶች በአሜሪካ ባለው መጥፎ የአየር ፀባይ የተነሳ በረራዎችን ሰርዘዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ በረራዎች ነው የተሰረዙት።

መረጃው ከቢቢሲ ነው የተገኘው።