በአሜሪካ የኢትዮጵያውያን የጊዜያዊ ከለላ መብት መነሳትን ለማስቆም ክስ መከፈቱ ተሰማ።
የትራምፕ አስተዳደር በሃገሩ ለሚኖሩ 5ሺህ ኢትዮጵያውያን ተሰጥቶ የነበረውን ከለላ ማንሳቱ ይታወሳል።
የአስተዳደሩን ውሳኔ ለማስቆም 3 ኢትዮጵያውያን አፍሪካን ኮሚዩኒቲስ ቱጌዘር ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ተቋም ጋር በመሆን በቦስተን ፍርድ ቤት ክስ መስርተዋል።
በክሱ “ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ባለችበት ሁኔታ ከለላው መቋረጡ ተገቢ አይደለም” ሲሉ አቅርበዋል።
አፍሪካን ኮሚዩኒቲስ ቱጌዘር ከዚህ ቀደም የደቡብ ሱዳን ዜጎች ከለላን በተመለከተ ወደዚሁ የቦስተን ፍርድ ቤት ጉዳዩን በማምጣት የትራምፕ አስተዳደር ውሳኔ እስኪታይ ድረስ እንዲታገድ ማስወሰኑ (https://t.me/tikvahethmagazine/26779) ይታወሳል።
መረጃው የሮይተርስ ነው።