ኢትዮጵያ፣ “ኦሪዮን-ኢ” የተሠኘውን ሩሲያ ሠራሽ ሰው አልባ ድሮን ታጠቀች ተባለ

ኢትዮጵያ፣ “ኦሪዮን-ኢ” የተሠኘውን ሩሲያ ሠራሽ ሰው አልባ ድሮን መታጠቋን የኢትዮጵያ መንግሥት ሰሞኑን ካዘጋጀው የድሮን ኤክስፖ ላይ ማረጋገጡን ዲፈንስ ብሎግ ዘገበ።

ኢትዮጵያ የታጠቀችው ሩሲያ-ሠራሹ ድሮን “ለዒላማ ቅኝት” እና “ለውጊያ” የሚውል መኾኑን ዘገባው ጠቅሷል።

ድሮኑ ከምድር ወለል በላይ እስከ 7 ሺሕ 500 ሜትር ከፍታ እና ለ24 መብረር እንደሚችል የሩሲያ የመከላከያ መረጃዎች ያመለክታሉ ተብሏል።

ሩሲያ ይህንኑ ድሮን ለመጀመሪያ ጊዜ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ሶሪያ እና ከዚያም ዩክሬን ላይ ለውጊያ ተጠቅማበታለች ያለው ዘገባው፣ ኾኖም ድሮኑን ለሌላ አገር መሸጧ በይፋ ሲረጋገጥ የኢትዮጵያው የመጀመሪያ መኾኑን ጠቅሷል።