የትራምፕ አስተዳደር “ጊዜያዊ ከለላ” ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ያሳለፈው ውሳኔ መነሻው “ፖለቲካ” እና “ዘረኝነት” ነው

“አፍሪካን ኮምኒቲስ ቱጌዘር” የተሠኘ አሜሪካ ውስጥ የተቋቋመ የመብት ተሟጋች ድርጅትና ሦስት ኢትዮጵያዊያን፣ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር “ጊዜያዊ ከለላ” ያላቸው ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ያሳለፈው ውሳኔ መነሻው “ፖለቲካ” እና “ዘረኝነት” ነው በማለት ለፍርድ ቤት አቤቱታ አስገቡ።

አመልካቾቹ፣ ፍርድ ቤቱ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ እንዲያግደው መጠየቃቸውን የዘገበው ሮይተርስ ነው። የአሜሪካ የአገር ውስጥ ደኅንነት መስሪያ ቤት ኢትዮጵያዊያኑ እስከ የካቲት 6 ከአሜሪካ እንዲወጡ ያዘዘው፣ ኢትዮጵያ “ከሰብዓዊ ቀውስ” ባልተላቀቀችበት ሁኔታ ነው በማለት አመልካቾቹ ተቃውመዋል ተብሏል።

አመልካቾቹ፣ ውሳኔው 5 ሺሕ ኢትዮጵያዊያን ጊዜያዊ ከለላቸውን እንዲያጡ ያደርጋል በማለት አቤቱታ በአቤቱታቸው ላይ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል ተብሏል።