የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያ እና ግብጽ በናይል ወንዝ ዙሪያ ከስምምነት ሊደርሱ ይችላሉ ብለው እንደሚያምኑ ትናንት ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታህ አል ሲሲ ጋር በነበራቸው ውይይት ላይ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ግድቡን የሠራችው ግብጻዊያን ውሀ በሚያገኙበት መንገድ ላይ ነው በማለት የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ፣ በግድቡ ምክንያት የናይል ወንዝ የውሀ ፍሰት ተገድቧል ብለዋል።
ግድቡ “ትልቅ ችግር” እንደሆነ በመጥቀስም፣ የሆነ ነገር ማድረግ እንደሚፈልጉ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኢትዮጵያንና ግብጽን ማሸማገል እንደሚፈልጉ ሲናገሩ የአሁኑ በዚህ ሳምንት ብቻ ሁለተኛ ጊዜያቸው ነው።