ከጋሼና ከተማ በቅርብ ርቀት የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ

ከጋሼና ከተማ በቅርብ ርቀት በምትገኘው እስታይሽ ከተማ ዙሪያ ፋኖ በወሰደው የስቦ መምታት እርምጃ 24 የብልፅግና መከላከያ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ታወቀ!

የጠላት ኃይልን ወደ ቀይ ዞን በመሳብና 360° ከበባ ውስጥ በማስገባት ፋኖ በወሰደው የአጭር ሰዓት ማጥቃት፡ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ከደረሰው ሰብአዊና ቁሣዊ ኪሳራ ባሻገር አገዛዙ አለኝ እያለ የሚመፃደቅበት ወታደራዊ ኃይል እራሱን ተከላክሎ ማዳን የማይችል እጅግ ደካማ ኃይል መሆኑ በገሀድ ታይቶበታል ብለዋል ወታደራዊ ተንታኞች።

የአንድነቱን ችቦ የለኮሰው የፋኖ ኃይል፡ የአማራ ሕዝብን ሕልውና ለማረጋገጥና ፍትሕ ርትዕ ለማስፈን እያካሄደው ባለው ጦርነት አገዛዙ ከሰማይ በራሪ እስከ ምድር ተምዘግዛጊ ሜካናይዝድ መሣሪያዎች አስታጥቆ የሚያሰልፋቸው ወታደሮችን ሲያሻው በደፈጣ፡ ሲያሰኘው በጨበጣ እየደመሰሰ ግብዓተ መሬታቸውን እየፈፀመ ይገኛል።