ሼህ አላሙዲ ከጃንሆይ ቤተሰቦች ላይ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን መግዛቱን ዛሬ አስታወቀ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ (ሼህ አላሙዲ) ከጃንሆይ ቤተሰቦች ላይ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን መግዛቱን ዛሬ አስታወቀ።

ሚድሮክ፣ ሆቴሉን ኢትዮጵያ ለምታዘጋጀው 32ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ተሳታፊዎች የማሪዮት ሆቴሎችን ደረጃ በጠበቀ መልኩ እንደሚያድሰው ገልጧል።

ሚድሮክ ሆቴሉን የገዛው፣ ሆቴሉን ከመንግሥት ገዝቶ በባለቤትነት ሲያስተዳድረው ከነበረው የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማኅበር (ከጃንሆይ ቤተሰቦች) ነው።

የዋቤ ሸበሌ ሆቴል የቦርድ ፀሃፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን፣ ሚድሮክ የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለመጭው ትውልድ ለማስተላለፍ መስማማቱን ገልጸዋል።

ሆኖም ሚድሮክ ሆቴሉን የገዛበትን ዋጋ ይፋ አላደረገም።