የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ፌደራል መንግሥቱ በሚፈጽማቸው “ሕገወጥ” እና “አድሏዊ” አሠራሮች ሳቢያ ትግራይ ከፌደራል መንግሥት ጋር ከሚያገናኛት የፊስካል ሥርዓት እንዳትገባ እያደረገች ትገኛለች በማለት ከሰሰ።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፌደራል መንግሥቱ ጥሏቸዋል ባላቸው ገደቦች እና አድልዖዎች ምክንያት ከፍተኛ የበጀት ጉድለት እያጋጠመው መሆኑን ዛሬ በመቀሌ ከተማ በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ገልጧል።
የብሔራዊ የገቢ አሰባሰብ ግብረ ሃይሉ ሰብሳቢ አብርሃም ተከስተ፣ በአገር ውስጥም ኾነ በውጭ አገር የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ በትግራይ ሕዝብ የውስጥ አቅም ላይ እንዲያተኩሩ ጥሪ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ጥሪ አቅርበዋል።