የፋኖን አንድነት በጉጉት ሲጠብቁ የነበሩት የአገዛዙ ወታደሮችም ጭምር ናቸው።
ፋኖ አንድ ወጥ ድርጅት መስርቶ አንድነቱን ባወጀ ማግስት የአገዛዙ ጦር በገፍ እየተናደ ፋኖን እየተቀላቀለ መሆኑ ታውቋል።
የፋኖን አንድ መሆን በጉጉት ሲጠብቅ የነበረው በመከራ ውስጥ የሚገኘው የአማራ ሕዝብና ሌሎች የዚህ ፀረ ሕዝብ ኦህዴድ መር ብልፅግና አገዛዝ ተጠቂ የሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ብቻ ሳይሆኑ አገዛዙን እያገለገሉ የሚገኙ ወታደሮችና ወታደራዊ አዛዦችም ጭምር ናቸው።
የአገዛዙ ወታደሮች በጉጉትና በተስፋ ሲጠብቁት የነበረው የፋኖ አንድነት የብስራት ዜና መሰማቱን ተከትሎ፡ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ከስምሪት ቀጠናቸው በመጥፋት በገፍ ፋኖን እየተቀላቀሉ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።