የከተራ እና ጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2018 የከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል።
የድርጅታችንን መመስረት ተከትሎ ሰራዊታችን፣ መላው የአማራ ህዝብ፣ የዳያስፖራው ማህበረሰብ እና የትግሉ ደጋፊወች በከፍተኛ ስሜት እና ደስታ መቀበላቸውን ስናረጋግጥ ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል። በአንድነታችን ከፍተኛ ልባዊ ደስታን የተጎናፀፈው ሰራዊት እና ህዝብ የድሉን ፅዋ ያነሳ ዘንድ የጠላትን አከርካሪ መስበር የሚችል ስልታዊ አመራር ለመስጠት መዘጋጅታችንን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሀገራችን ባህል እና ትውፊት እንዲጠበቅ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባህሉን እና እምነቱን በነፃነት የሚያራምድበት ሀገር እንዲኖረን የጀመረውን ፀረ አገዛዝ ተጋድሎ በአዲስ መንፈስ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን።
መላው ሰራዊታችን እና አመራሩ በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ሁሉ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር እንድትሰሩ እናሳስባለን።
በድጋሚ መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ/አፋብን/