ተጠናክሮ በቀጠለው የህልውና ተጋድሎ አራት መቶ አለቃ ማዕረግ ያላቸውን ጨምሮ 34 የጠላት ኃይል በመደምሰስና 21 ክላሽንኮፍ በመማረክ ተከዜ ክፍለ ጦር ታላቅ ጀብዱ ፈፀመ!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ክንፍ የሆነው ተከዜ ክፍለ ጦር ከጥር 08 እስከ ጥር 10/ 2018 ዓ/ም ለተከታታይ ሦስት ቀናት ከጠላት ጋር ባደረገው እልህ አስጨራሽ ተጋድሎ የላስታ ሰንሰለታማ ተራሮች የጠላት መቀበሪያ የወገን ከለላና መከታ ሆነው ተከዜዎቹ የብልፅግናን ወንበር አስጠባቂ ምስለኔ አንገት በማስደፋት ታላቅ ጀብዱ ፈፅመዋል።
ጠላት በሜካናይዝድ የታገዘ በመድፍ፣ በ107 ፣በዙ-23(አየርመቃወሚያ)፣በሞርታር-120፣በሞርታር-82 ታግዞ ከላስታ ወረዳ ኩልመስክ ዙሃባ-ኪዳነ ምህረት እና ከገነተማርያም ቻይና ካምፕ ቀጭንአበባ ደባራይ ድረስ ያካለለ አውደ ውጊያ ያደረገ ሲሆን ተከዜዎቹ በሚያውቁት መልከዓምድር በመውጣትና በመውረድ ጠላትን ሲያደባዩት ውለው አድረዋል።
በዚህ አውደ ውጊያ አራት የመቶ አለቃ ማዕረግ ያላቸው አመራሮችን ጨምሮ 34 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ ከ20 በላይ መቁሰላቸው ታውቋል፤በተያያዘም 21 ክላሽንኮፍ፣685 የድሽቃ ተተኳሽ፣520 የብሬን ተተኳሽ፣760 የክላሽ ተተኳሽ፣18 የእጅ ቦምብ፣26 የደረትና የወገብ ትጥቅ ተማርኳል።
ድንጋጤ ውስጥ የገባው የብርሃኑ ጁላ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት ከፋኖም ጭምር መልከዓምድሩም እየተዋጋኝ ነው በማለት የአማራ መሬቶችን በመድፍ፣በ107፣በሞርታርና በዙ-23 በመደብደብ ለዘመናት ተጠብቆ የነበረውን የእመኪና መድሃኒአለምን ጥብቅ ደን እና ከአንድ አካባቢ የሚገኙ የአምስት አርሶ አደር ቤቶችንና ሙሉ ንብረት ማቃጠሉና ማውደሙ ታውቋል።
በመጨረሻም ለአመታት ስንናፍቀው የነበረው እና ደማችን አፍስሰን አጥንታችን ከስክሰን ያፀናነው አንድ አታጋይ ድርጅት ለጠላቶቻችን የሞት ደብዳቤ ለአማራውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የነፃነት ቁልፍ ለሆነው የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስረታ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን፤ይህንን ድርጅት እንደ አይናችን ብሌን እንድንጠብቀውና እንድንንከባከበው እንዲሁም በዱሩ በገደሉ እየተዋደቃችሁ እየታገላችሁ ለምትገኙ ለሁሉም የፋኖ አባላትና አመራሮች እንኳን ለከተራና ጥምቀት በዓል አደረሳችሁ ሲል የተከዜ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ