የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ ሕወሓት በእንዳሥላሴ ከተማ በሚገኙ የተፈናቃዮች መጠለያዎች በግዳጅ መዋጮ እየሰበሰበ መኾኑን በመግለጽ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ቅሬታ አቅርቧል።
የሕወሓት ባለሥልጣናት ከተፈናቃዮች በነፍስ ወከፍ 200 ብር በግዳጅ የሚሰበስቡት፣ ፓርቲውን ለማዳንና ለፓርቲው 50ኛ ዓመት በዓል ማክበሪያ በሚል ምክንያት እንደኾነ ተገልጧል።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሕወሓት አስገዳጅ መዋጮ መጣል እንደማይችል ገልጦ፣ የአካባቢው መንግሥታዊ አካላት ድርጊቱን እንዲከታተሉ አሳስቧል።
ሕወሓት በግዳጅ መዋጮ መሰብሰቡን አስተባብሎ፣ ኾኖም ማንም ሰው ለፓርቲው በፍላጎቱ መዋጮ ማዋጣት ይችላል በማለት ምላሽ ሰጥቷል።