ሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተጽዕኖ ለመቀነስ ከግብጽ እና ሶማሊያ ጋር ወታደራዊ ቅንጅት ለመፍጠር ዝግጅት እያደረገች መኾኗ ተሠማ።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ ይህንኑ የወታደራዊ ቅንጅት ስምምነቱን ለማጠናቀቅ በቅርቡ ወደ ሪያድ እንደሚጓዙ ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ብሉምበርግ ዘግቧል።
ሶማሊያ እና ግብጽ ቀደም ሲል የወታደራዊ ትብብር ስምምነት አላቸው።
ሳዑዲ ዓረቢያ ከሶማሊያ እና ግብጽ ጋር የወታደራዊ ቅንጅት ስምምነት ለመፈራረም የወሠነችው፣ ኢምሬቶች በሶማሊያ መንግሥት ትዕዛዝ ሶማሊያ ውስጥ እንዲሁም በሳዑዲ ዓረቢያ ትዕዛዝ ደቡባዊ የመን ውስጥ ወታደሮቿን ማስወጣት መጀመሯን ተከትሎ ነው።