አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ከዚህ አለም በሞት ተለየ፡፡
በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነቱና በተዋናይነቱ የሚታወቀው ነፃነት ወርቅነህ በሌሎችም የጥበብ ስራዎቹ በኪነ – ጥበቡ ዘርፍ ታዋቂነትን አትርፏል፡፡
በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈውን የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅ ሆኖ ለዓመታት ሲሰራ መቆየቱም ይታወሳል፡፡
አርቲስቱ በደረሰበት ህመም ዛሬ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ተናግሯል፡፡
አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ባለትዳር እና የ3 ልጆች አባት ነበር፡፡
mereja.com ለቤተሰቦቹ እና ለወዳጆቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
