የዘንድሮዋ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሽልማቷን ለዶናልድ ትራምፕ ሰጠች።

የዘንድሮዋ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሽልማቷን ለዶናልድ ትራምፕ ሰጠች።

የዘንድሮዋ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆነችው ቬኔዙዌላዊቷ ተቃዋሚ  ማሪያ ኮሪና ማቻዶ (https://t.me/tikvahethmagazine/26067) ወደ ነጩ ቤተመንግስት በማቅናት ሽልማቷን ለዶናልድ ትራምፕ ሰጥታለች።

ዶናልድ ትራምፕ አቆምኳቸው ያሏቸውን ጦርነቶች በመዘርዘር ሽልማቱ እንደሚገባቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ የሚታወስ ሲሆን ያገኙት ግን ከኖቤሉ ይልቅ ከፊፋ የተሰጣቸውን አዲሱን የሰላም ሽልማት ብቻ ነው።

ትሪምፕ ” ማሪያ ለሰራሁት ስራ የኖቤል የሰላም ሽልማቷን ሰጥታኛለች” ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያቸው በመፃፍ ሽልማቱን መቀበላቸውን አረጋግጠዋል።

ኋይት ሃውስም ሽልማቱን ሲቀበሉ የሚያሳይ ምስል አጋርቷል።

የኖቤል ኮሚቴ ከቀናት በፊት ዜናው ከተሰማ ወዲህ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ መስጠቱ ሲታወስ ኮሚቴው የሽልማቱ አሸናፊ አንዴ ከተገለጸ በኋላ ሽልማቱ የማይሻር እና ወደ ሌላ ሰው የማይተላለፍ እንደሆነ ገልጾ ነበር።