ግብጽ፣ ሶማሊያ ውስጥ የተሠማሩ ወታደሮቿ ለፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ መንግሥት ጥበቃ ማድረግ ተቀዳሚ ተግባራቸው እንዲኾን ማድረጓን ዘ ናሽናል ጋዜጣ ዘገበ። የግብጽ መንግሥት፣ ለሶማሊላንድ እውቅና የሠጠችው እስራኤል ከባላንጣዋ ኢትዮጵያ ጋር ጥብቅ ቀጠናዊ አጋርነት በመፍጠር፣ ግብጽ በሶማሊያ እና በደቡባዊ ቀይ ባሕር አካባቢ ተጽዕኖ እንዳይኖራት ልታደርግ ትችላለች የሚል ስጋት እንዳላት ከውስጥ አዋቂ ምንጮች መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል። እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና ከሠጠች በኋላ፣ ግብጽ ሶማሊያ ውስጥ ያሏትን የወታደራዊ እና የጸጥታ ግቦች እንዲሁም የወታደሮቿን ስምሪት መከለሷን ምንጮች እንደነገሩት የዜና ምንጩ አመልክቷል። ግብጽ ከአንድ ዓመት በፊት ከሶማሊያ ጋር የወታደራዊ ትብብር ስምምነት የተፈራረመች ሲኾን፣ ለፕሬዝዳንት ሞሃመድ መንግሥትም የጦር መሳሪያ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች። https://miniliksalsawi.substack.com/p/cairo-fears-breakaway-region-could