በወልድያ ዙሪያና በቃሊም በተደረገው ተጋድሎ ፋኖ ስኬታማ ጥቃቶችን በመሰንወር ድል ተቀዳጅቷል!

በወልድያ ዙሪያና በቃሊም በተደረገው ተጋድሎ ፋኖ ስኬታማ ጥቃቶችን በመሰንወር ድል ተቀዳጅቷል!

የሐውጃኖ ክፍለ ጦር ጥር 5/2018 ዓ.ም ንጋት ጀምሮ ከአሳምነው ክፍለ ጦር ጋር በመጣመር ወልድያ ዙሪያ እና ቃሊም በመካናይዝድና በድሮን የታገዘ የጠላት ሃይል ጋር ተጋድሎ በማድረግ በጠላት ላይ የተለመደውን ገድላቸውን በመፈፀም ታላቅ ድል ተቀዳጅተዋል:::

የአብይ አህመድ የዙፋን ጠባቂ ሰራዊት በድሮን፣ በመድፍ፣ በታንክና በሞርታር ታግዞ የከፈተውን መጠነ ሰፊ ጥቃት የሐውጃኖ አንበሶች በላቀ ወታደራዊ ጥበብ መክተው በማክሸፍና ከባድ መልሶ ማጥቃት በማድረግ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ታላቅ ድል ተጎናፅፈዋል::

​ጥር 5/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 የተጀመረውና እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ለ13 ሰዓታት ያህል ያለማቋረጥ ሲካሄድ የዋለውና ጠላት በመቶዎች ሙትና ቁስለኛ እንዲሁም ምርኮኛ በሆነበት እጅግ ከባድ ፍልሚያ በሐውጃኖ ክፍለ ጦር ሙሉ የበላይነት ተጠናቋል።

በታሪካዊው የአውደ ውጊያ ግንባር ጀግናው የሐውጃኖ ክፍለ ጦር በአርበኛ ካሳ አበበ እና በምክትሉ አርበኛ ደሳለኝ መራጊያው እየተመራ ከምስራቅ አማራ ኮር አንዱ መንትያው አሳምነው ክፍለ ጦር ጋር ጎን ለጎን ተሰልፎ በቃሊም ሚጦ በኩል ባደረገው ከባድ ማጥቃት፣ በከፍተኛ ዘመናዊ ትጥቅ የታገዘውን የጠላት ኃይል በከበባ ውስጥ አስገብቶ እንደ ቅጠል አርግፎት ውሏል::

​በዚህ ታሪካዊ ፍልሚያ የተገኙ ድሎች፦
👉​የሰው ኃይል ኪሳራ፦ በጠላት ወገን ላይ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙትና ቁስለኛ ተመዝግቧል። በሐውጃኖ ክፍለ ጦር እና አሳምነው ክፍለ ጦር ጥምረት በመቶዎች የሚቆጠር ጠላት ሙትና ቁስለኛ ብሎም ምርኮኛ ሆኗል::

​የተማረኩ ትጥቆች፦
👉​ 8  ክላሽ
👉​1100 የሚደርስ የተለያየ አይነት ተተኳሽ
👉20 የክላሽ ካዝና
👉5 የሞርተር ቁንቡላ
👉የሰው ሃይል ሙሉ ዶክሜንት