ካላኮርማ ክፍለ ጦር ጉባላፍቶ እና ራያ ቆቦ ወረዳ በሁለት ግንባር ከባድ ውጊያ በማካሄድ ድል አስመዘገቡ::
ምስራቅ አማራ ኮር 2 ካላኮርማ ክፍለ ጥር 5/2018 ዓ.ም ጦር ጉባላፍቶ ወረዳ በቅሎ ማነቂያ እና ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ በሁለት ግንባሮች ከባድ ውጊያ በማካሄድ በርካታ ጥምር ዙፋን ጠባቂ አገር አፍራሽ የጠላት ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድል አስመዝግበዋል::
ካላኮርማ ክፍለ ጦር 2ኛ እና 3ኛ ሻለቃ ከእንጃፋት ወንዳች ኩልመስክና ድልብ የመጣንና በቅሎ ማነቂያን ይዞ ወደ ቃሊም ማጥቃት ያደረገን ጠላት ባግባቡ መክተው በመዋልና በርካታ ሰራዊቱን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ብሎም ምሽግ ያደረገውን በቅሎ ማነቂያ ከተማና ዙሪያውን በማስለቀቅ ወታደራዊ ገዥ መሬት መቆናጠጥም ችለዋል::
በሌላኛው ግንባር ካላኮርማ ክፍለ ጦር 1ኛ እና 4ኛ ሻለቃ እንዲሁም የ5ኛ ሻለቃ ቃኝ ጥር 5/2018 ዓ.ም ቀትር አካባቢ ጀምሮ ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ድረስ ዘልቀው በመግባት በርካታ የፋሽስቱ አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ላይ ከባድ ጥቃት በማድረስ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ጀብድ ፈፅመው ድል አስመዝግበዋል::
በዚህም የምስራቅ አማራ ኮር ሁለቱ ካላኮርማ ክፍለ ጦር በሁለት ግንባሮች ከባድ ተጋድሎ በማድረግ ቃሊምና ወልድያ ዙሪያ ከባድ ትንቅንቅና ተጋድሎ ካደረጉት ከምስራቅ አማራ ኮር አንድ አሃዶች ጋር የተናበበና የተቀናጀ ሚዛን ጠባቂ ግዳጅ በመፈፀም አመርቂ ድል አስመዝቧል::
የፋኖን ክንድ መቋቋም ያቃተው የፋሽስቱ ብልፅግና አገዛዝ ጥምር ሰራዊት ራያ ቆቦ ሮቢት ከተማ ያልታጠቁ ንፁሃን አማራዎችን በግፍ ረሽኗል::
አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ