በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሰፈሮች ከባድ ውጊያ ተቀስቅሶ ዋለ!

በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሰፈሮች ከባድ ውጊያ ተቀስቅሶ ዋለ!

በከተማዋ ስር በሚገኙ ሁለት ክፍለ ከተሞች ላይ ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ እስከምሽት በዘለቀው ውጊያ፡ ፋኖ አማራዊ ጀግንነትን ከጦር ሣይንስ እውቀት ጋር ያጣመረ ነው የተባለ ማጥቃት በመሰንዘር ውጊያውን በበላይነት ተቆጣጥሮ ድል መቀዳጀቱ ለማረጋገጥ ተችሏል።

አገዛዙ በውጊያው ከከባድ መሣሪያ ጀምሮ በሚኒሻና አድማ ብተና አባላት መንገድ መሪነት ኤሊት ፎርስ ብሎ የሚጠራቸውን በርካታ አየር ወለድ ኮማንዶዎችን ያሰለፈ ቢሆንም፡ ነገር ግን የፋኖን ጥቃት መቋቋም አቅቷቸው ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ ኪሣራን ተከናንበዋል።