ጥንታዊነት እስከ ዘመናዊነት Antiquity to Modernity በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ
ቀሲስ አስተርአየ በቅርቡ ዶ/ር ጌታቸው መታፈሪያ ባስመረቁት መጽሐፍ ላይ ጥንትነትና ዘመናዊነት (antiquity to modernity) በሚል ርዕስ ረዘም ያለ ጥልቅ ይዘት ያለው ጽሑፍ አቅርበዋል። ዋናውን የዶ/ር ጌታቸውን መጽሐፍ አግኝተን ባናነበውም ቀሲስ አስተርአየ መጽሐፉን ተንተርሰው የሰጡት ትንታኔ መጽሐፉን ለማግኘት እንድንቸኩል አድርጎናል። ከቀሲስ ጽሑፍ እንደተረዳነው በቤተ እስራኤልና በኦርቶዶክስ ሕዝበ ክርስቲያኑ ሲካሄዱ የኖሩት ዕሴቶች ኢትዮጵያ የተገነባችባቸውና አሁን የፈረሱትን ዕሴቶች እንደሆኑ የሚያስረዱ ናቸው።
እነዚህ ፈረሱ እየተባሉ በፖለቲከኞች የሚለፈፉትና ተመልሰው የሚገነቡት ዕሴቶች ምን እንደሆኑ ተገልጸው ሲነገሩ የተሰሙ አይደሉም። ፋኖነትና አርበኝነትም በተባራሪ ሲነገሩ ይሰማሉ እንጅ መነሻቸው አልተገለጸም ነበር። ቀሲስ መላልሰው ቢናገሩትም የቤተ ክርስቲያንን ውለታ መንካት የሚጸየፉ ፖለቲከኞች የተቀደሙ እየመሰላቸው እንዳላዩ ይሸሹታል። በነገራችን ላይ በቀሲስ የሚቀርቡትን ይህን የመሰሉትን ሀሳቦች ማንበብና ለህዝብ ማዳረስ የሚገባቸው ቀሳውስት፣ ጳጳሳትና ቆሞሳትና ቀሳውስት ሰባኪዎች ነበሩ። በቅኔውና በዘመኑ እውቀት ያልበሰሉ አስመሳዮችና ጥራዝ ነጠቆች እንጅ እንደቀሲስ አስተርየ እርቀውና ዘልቀው ስላልሄዱ የራሳቸውንም አላዋቂነት የሚያጋልጣቸው ስለሚመስላቸው ይደብቁታል ወይም ለመረዳት ካቅማቸው በላይ ይሆንባቸዋል። ለማንኛውም ሙሉውን የአስተሳሰብን ክህሎትን የሚያዳብረውን የቀሲስን ጽሁፍ ከዚህ በታች አቅርበንላችኋል። ጥንታዊነት እስከ ዘመናዊነት Antiquity to Modernity በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ