ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ)  ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ወታደራዊ አዛዥ  እና የግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ አጠር ያለ መግለጫ!!

ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ)  ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ ወታደራዊ አዛዥ  እና የግዙፉ ላስታ አሳምነዉ ኮር ሰብሳቢ አርበኛ ወንድሙ ማሩ በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ አጠር ያለ መግለጫ!!

ይህን የአማራ ፋኖ ትግል የጀመርንበት ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩንም  ዋነኛ ምክንያታችን አማራ በመሆናችን ብቻ በወለጋ ፣ በነቀምት ፣በሻሸመኔ፣ በጉራፈርዳ ፣በመተከል እና በሌሎች አካባቢዎች በጃምላ ተጨፍጭፈናል በጅምላ ተገለናል ፣ በጅምላ ተፈናቅለናል  በዚህም ምክንያት አማራ የመዳኛ መንገዱ ክንዱና ነፍጡ መሆኑን አዉቀን ዱር ቤቴ ካልን 3 እና 4 ዓመታትን አሳልፈናል። በዚህም ቆይታችን ዱላ ይዘን ወጥተን ከክላሽ እስከ እስከ ዲሽቃ ከዲሽቃ እስከ ሞርተር እና ሌሎች ካባድ መሳርያዎችን ታጥቀናል።   ይህን ሁሉ መሳርያዎች ይዘን እየታገልን ባለንበት ወቅት  በ አባታችን ብ/ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ስም ሲነግድ የነበርዉ ኮረኔል ፈንታሁን ሙሃቤ በትላንትናዉ ዕለት ለዚህ ፋሽዝም ስርዓት እጅ ሰጠ የሚል ዜና ሰምተናል። ኮረኔል ፈንታሁን ለአገዛዙ እጅ ሰጠ አልሰጠ የአማራ ፋኖ ትግል አይቆምም ምክንያቱም ይህ ትግል ለግለሰቦች ስንል ሰላልወጣን።  እኛ ግን የጀኔራል አሳምነዉ ልጆች የአባታችን የአደራ ቃል ተወጥተን የአማራን ትንሳኤ እናበስራለን። 
አሁንም በዚህ ትግል እሚነግድ ካለ መንገዱ ክፍት ነዉ እንክርዳዶቹ ከስንዴዉ እንድትለዩልን እንፈልጋለን።

ይህን ትግል ስንጀምር  ላንጨርስ አልጀመርነዉም አማራነት ያሸንፋል ድል ለፋኖ ድል ለአማራ!!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒልክ ዕዝ ም/ወታደራዊ አዛዥ እና የግዙፉ  ላስታ አሳምነው ኮር ሰብሳቢ  አርበኛ ወንድሙ ማሩ!!