ኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሴት ተራራ ላይ በሚገኘው ጫካና ባካባቢው መንደሮች ላይ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሰደድ እሳት ለቀውበታል በማለት ትናንት ምሽት ባሠራጨው መግለጫ ከሷል።
ቡድኑ፣ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት ሙከራ ባደረጉ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ብሏል።
የመንግሥት ኃይሎች በጫካው ላይ ኾነ ብለው ሰደድ እሳት የለቀቁት ተዋጊዎቹን ለማጥቃት እንደኾነ የገለጠው ቡድኑ፣ የመንግሥት ኃይሎች በቄለም ወለጋ ዞን በተመሳሳይ ጫካዎችንና መንደሮችን በእሳት አያይዘዋል በማለት ወቅሷል።