በምስራቅ አማራ ቀጠና እየተገባደደ በሚገኘው ታህሳስ ወር ብቻ አንድ ጄነራል መድፍን ጨምሮ ሦስት የአየር መቃዎሚያ በፋኖ ወድሟል!
በቀጠናው የቀረው የጠላት ሜካናይዝድ መሣሪያም “ይዘገያል እንጂ አህያ የጅብ ናት” ነው እጣፈንታው ተብሏል።
በምስራቅ አማራ ቀጠና በክቡር ሰማዕቱ አርበኛ አደም አሊ(አባናደው) ስም በተሰየመው ወታደራዊ ዘመቻ 3ሺ ሦስት(3003) ወታደሮቹ በፋኖ የተገደሉበት እና 679 ወታደሮቹ ደግሞ የተማረኩበት በአሰፋ ቸኮል የሚመራው የሰሜን ምስራቅ ዕዝ፡ አሁን ደግሞ የዕዙ ሜካናይዝድ ክፍል አለኝ ከሚለው ከባባድ የጦር መሣሪያ መካከል አንዱና አዲሱ የአየር መቃዎሚያ በፋኖ በላውንቸር ተመቶ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
ሰሞኑን የክልሉ ፖሊስ አባላትን ባህርዳር ላይ ሰብስቦ “ፋኖን ያጀገነው እኛ ባለመተባበራችን እንጂ፡ ፋኖ አቅመቢስ ነው” በሚል ሲፎክር በነበረው፡ ከወራት ወዲህ ደግሞ የቅርብ ጓዶቹ “የባዶ ዕዝ አዛዡ” በሚል ስላቅ በሚጠሩት በአሰፋ ቸኮል የሚመራው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ፡ “ዘመቻ አባናደው” ከመስከረም 14/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀናት ከመካሄዱ በፊት ማለትም ነሐሴ 03/2017 ዓ/ም አንድ ዙ 23(የአየር መቃዎሚያ) ራያ ቆቦ ሮቢት ላይ በፋኖ እንደተማረከበት በእለቱ መረብ ሚዲያ በምስል አስደግፎ መዘገቡ አይዘነጋም።
ይኸው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ከዘመቻ አባናደው በኋላ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ የነበረ ሲሆን፡ ከመማረክና ከመደምሰስ የተረፉ የዕዙ ሰራዊት አባላትን በቡርቃ ማሰልጠኛ ጣቢያ የአካልና የስነ ልቦና ተሀዲሶ ስልጠና ለወራት በመስጠት ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም አስመርቆ ነበረ።
ለወራት የተሀድሶ ስልጠናው የተሰጣቸው የዕዙ ሰራዊት አባላት፡ ከነ አዛዦቻቸው ሲጠሉት የነበረውን ልሙጡን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን በምረቃ ስነስርዓታቸው ላይ ከላይ እስከታች ለብሰው ትርኢት ማሳየታቸው ብዙዎችን ያስገረመ ሲሆን፡ “በዘመቻ አባናደው የደረሰባቸው ከባድ ጉዳት የናቁትን ባንዲራ አክብረው እንዲለብሱ አድርጓቸዋል” ሲሉም ጉዳዩን በትዕዝብት የተመለከቱ አንዳንድ ሰዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
ይሄው ዕዝ ሰራዊቴን የተሀድሶ ስልጠና ሰጥቼ በተሰጠኝ የግዳጅ ቀጠና አሰማራሁ ባለ ማግስት ደግሞ የአየር መቃዎሚያው ከነ ኦራሉ በደቂቃዎች ልዩነት ወደ አመድነት ተቀይሮበታል።
ዕዙ አለኝ የሚለው ከባድ መሣሪያው ከነ ኦራሉ የወደመው ትናንት ታህሳስ 25/2018 ዓ/ም ከወልድያ ጥቁር ውሀ በቅርብ ርቀት ቃሊም መገንጠያ አከባቢ ልዩ ቦታው ዘንዶ ጅራት ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ የምኒልክ ዕዝ ፋኖ በፈፀመበት የላውንቸር ጥቃት ነው።
በዚኸው ሰሜን ምስራቅ ዕዝ ስር 803ኛ ኮር
ታህሳስ 07/2018 ዓ/ም በላስታ ግንባር ከወደ ፋኖ በተፈፀመበት ጥቃት አንደኛው የአየር መቃዎሚያ በድሽቃ ተመቶበት ከጥቅም ውጭ ተደርጎበታል።
ጥቃቱ የተፈፀመው የአገዛዙ ኃይል የላሊበላ ከተማ አስተዳደር፣የላስታ ወረዳና የቡግና ወረዳ የካቢኔ አባላትን በዙ23 አጅቦ ከጋሸና ወደ ላሊበላ ከተማ እየተጓዘ እንዳለ ሲሆን፡ በዚህም የአየር መቃዎሚያው በፋኖ ዲሽቃ ተመቶ ከጥቅም ውጭ መደረጉን በወቅቱ መረብ ሚዲያ መዘገቡ ይታወሳል።
በተመሣሣይ ታህሳስ 20/2018 ዓ/ም አመሻሹን በአምባሰል ግንባር ግሸን ደብረ ከርቤ ዙሪያ ፋኖ በፈፀመው ደፈጣ ጣቃት አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ታጅቦበት የነበረ የአየር መቃዎሚያ በፋኖ ቦምብ ተመቶ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ታውቋል።
ዙ23ቱ ከሰሜን ምስራቅ ዕዝና ከሌሎች ዕዞች ተወጣጥታ በቅርቡ የተቋቋመችው የ11 ዕዝ ንብረት እንደሆነም ነው የተነገረው።
በተጨማሪም ታህሳስ 17/2018 ዓ/ም ፋኖ በፈፀመው ስኬታማ የሞርተር ጥቃት፡ ንፁኋንን ለእልቂት ሲዳርግ የነበረው የአገዛዙ ጄነራል መድፍ ከነ ተተኳሹ ዶግ አመድ የተደረገ ሲሆን፡ አራት የመድፍ ተኳሾች በሞርተር ቅንቡላ ፍንጣሪ ተመተው ሕይወታቸው አልፏል።
አገዛዙ በአምባሰል ግንባር በታሪካዊቷ ውጫሌ ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው ደንካ ሚካኤል ላይ መድፍ አጥምዶ የዘፈቀደ ድብደባ በመፈፀም የበርካታ ንፅኋንን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ አያሌ ሀብት ንብረት ሲያወድም መቆየቱን መረብ ሚዲያ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም።
በምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ስር በሞርተር ተኩስ ኢላማ “የሞርተር ቅምቡላን ከጥላት ኪስ ውስጥ መክተት ይችላሉ” የሚባልላቸው የኮሩ ሜካናይዝድ ክፍል ምድብተኞች፡ በፈፀሙት ስኬታማ የሞርተር ጥቃት ነው የጠላት መድፍ ከነ ተተኳሹና ተኳሾቹ የወደመው።