ደብረሲና ከተማ ዘልቀው የገቡት የፋኖ አባላቱ ከባድ ኪሳራ በማድረስ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡ ታወቀ!

ዛሬ ከንጋት ጀምሮ በደቡብ አማራ ሸዋ ቀጠና ደብረሲና ከተማን ጨምሮ በሾላ ሜዳ፣ በአርማኒያና ጭራ ሜዳ ላይ በተደረገ ትንቅንቅ ፋኖ በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ በማድረስ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡ ታወቀ!

ወደ ደብረሲና ከተማ ዘልቀው የገቡት የፋኖ አባላቱ፡ በከተማዋ የአየር ወለድ ኮማንዶዎች የሰፈሩበትን ካምፕ በማፈራረስ በርካታ ኮማንዶዎችን ሙትና ቁስለኛ ማድረጋቸውን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

ፀረ አማራው የብልፅግና ቡድን የፋኖን ጥቃት ለመመከት ከአየር ኃይልና ባሕር ኃይል ጀምሮ የአየር ወለድ ኮማንዶዎቹን፣ መሠረታዊ ወታደሮቹንና ሌሎች ታጣቂዎቹን ያሰለፈ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ሁሉ ግብስብስ ኃይል የፋኖን ግስጋሴ ሊያስቆም እንዳልቻለ ነው የተነገረው።