የአብይ አህመድ የጥገት ላም የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ

የአብይ አህመድ የጥገት ላም የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የአገልግሎት ታሪፍ  ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ
የሳፋሪ ኮምን ብስጭት፣ የሩቶን ቁጣ፣ የሰሞኑን የቴሌኮም ገበያን ንትርኮችን የአይ ኤም ኤፍ ግፊት ተከትሎ ኩባንያው በተለያዩ አገልግሎቶች ላይ ያደረገው አማካይ የ ዋጋ ጭማሪ የ23% በመቶ እንደሆነ ሰምተናል።
ኢትዮ ቴሌኮም ይህን የታሪፍ አገልግሎት ጭማሪ ያደረኩት፤ ተለዋዋጭ የ ማክሮ ኢኮኖሚ ፤ የካፒታል እና የስራ ማስኬጃ ወጭዎች ከፍ በማለቱ ነው ሲል ችግሮቹን ለመደባበቅ ጥሯል።
ከዚህም ባለፈ ኩባንያው፤ የአገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ የታሪፍ ጭማሪ አድርጌያለሁ ብሏል።
በዚህም መሰረት የ ዋጋ ጭማሪ ከተደረገባቸው አማካይ 23 በመቶ ውስጥ የቴሌብር ልዩ ስጦታ ጥቅል የ10% ቅናሽ ወደ 20% ከፍ ብሏል።
ኩባንያው ካሉት አብዛኛው ጥቅሎች ላይ 38 የተለያዩ ጥቅሎች ላይ ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ አላደረኩም ሲል ዋሽቷል።
ከዚህ ውስጥም በውስጥ አሰራር በደቂቃዎች ላይ ሽፍጥ የተሰራባቸው የ1 ብር፣ የ2 ብር፣ የ5 ብር እና የ1 ሰዓት ጥቅሎች ባሉበት እንዲቀጥሉ ወስኛለሁ ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
በተመሳሳይ የኢትዮዽያን የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ሁለተኛ አቅራቢ ሆኖ የተቀላቀለው ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ የታሪፍ ጭማሪ ማድረጉ ይታወቃል።
ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ ይህንን ጭማሪ ያደረገው በተመሳሳይ የኢንቨስትመንት እና የኦፕሬሽናል ወጪዎች ከፍ ማለታቸውን ተከትሎ እንደሆነ ሰምተናል።
ሳፋሪኮም ኢትዮዽያ በበኩሉ በአገልግሎቶቹ ላይ ከ 20 በመቶ ጀምሮ እንደየደረጃው እስከ 80 በመቶ ጭማሪ ማድረጉ ይታወቃል፡፡