በምኒልክ ዕዝ እና በላይ ዕዝ ጥምረት 197 የአገዛዙ ሰራዊት የተደመሰሰበትና ከ85 በላይ የቆሰለበት እንዲሁም ሁለት ብሬን እና 43 ክላሽ የተማረከበት ድል ተጎናፀፉ::

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ላስታ ጄኔራል አሳምነዉ ፅጌ ኮር በአርበኛ አምሳ አለቃ ጌታየ ተፈሪ የሚመራው ጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦርና ዋግሹም ብርጌድ እንዲሁም አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ኮር የተውጣጡ የፋኖ ኃይሎች በጥምረት ባደረጉት አውደ ውጊያ አብዛሀኛው የጠላት ኃይል የተደመሰሰበትና ይዞት የመጣው የጦር መሳሪያ ምርኮ የሆነበት ፋኖዎች ታላቅ ድል ያስመዘገቡበት አውደ ውጊያ ተካሂዷል።

ታህሳስ 19/2018 ዓ/ም ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ኃይል በሻምበል ጫላ የሚመራው 61ኛ ክፍለ ጦር መነሻውን ከቡግና ወረዳ አይና ከተማ ሀሙሲት አድርጎ ብርኮ ገብርኤል አመታዊ ንግስ በዓል በሚከበርበት በአራት አቅጣጫ ማለትም በብርኮ ገብርኤል አቅጣጫ፣በጤና ጣቢያው አቅጣጫ፣በጭቃው አቅጣጫ እና በብርኮ ኪዳነ ምህረት አቅጣጫ ለማጥቃት አስቦ ተኩስ የጀመረው የአገዛዙ ኃይል ለወሬ ነጋሪ ሳይቀር በመጣበት ላይመለስ ተደምስሷል።

በዚህ አውደ ውጊያ ጠላት በሜካናይዝድ የታገዘ አንድ ዙ-23፣ሁለት ሞርታር፣ሦስት ዲሽቃና ብዛት ያለው ብሬንና ስናይፐር ታግዞ የገጠመ ሲሆን የጦር ጠበብቶቹ ጠላትን በመጣበት ቋንቋ አናግረው ጄኔራል አስታጥቄ የላከውን ተረካክበው ከንፍሮ ጥሬ እንዲሉ የተረፈው ወደ መጣበት እየተዝረከረከ ተመልሷል።

ጠላት በተወሰደበት እርምጃ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያስተናገደ ሲሆን 197 ጠላት የ61ኛ ክፍለ ጦር የሰው ኃይልን ጨምሮ ሲደመሰስ፣85 ቁስለኛ እና ሰባት ተማርኳል፤ በተጨማሪም ሁለት ብሬን፣43 ክላሽ፣84 ወታደራዊ ሻንጣ፣2850 የብሬን ተተኳሽ፣2200 የክላሽ ተተኳሽ ተማርኳል።

ለአማራ ህዝብና ለንፁሃን የማይጨነቀውና የጦር ወንጀል እየሰራ የሚገኘው የብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ሰራዊት በየ ዓመቱ ታህሳስ 29 የሚከበረውን የቅዱስ ላሊበላ የልደት ቀንና የገና በዓል ንግስን ለማክበር እየተጓዙ የነበሩ 12 ንፁሃንን፣በሞርታር ቅንቡላ ሁለት ንፁሃንን፣ቤት ለቤት በመዞር የፋኖ መረጃ ናችሁ በሚል ሁለት እናቶችን ሲረሽን፣ ዘጠኝ ንፁሃንን አቁስሏል፤ ብርኮ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በመድፍ ቅምቡላ አፍርሷል።