ብልፅግና የሚኩራራባቸው መድፎችና አየር መቃዎሚያዎች ልክ እንደ ጧፍ ነደው ማለቅ ጀምረዋል!

ብልፅግና የሚኩራራባቸው መድፎችና አየር መቃዎሚያዎች ልክ እንደ ጧፍ ነደው ማለቅ ጀምረዋል!

አገዛዙ አሉኝ ከሚላቸው መድፎች መካከል ዋናውና ቀዳሚው ጄነራል መድፍ በፋኖ ሞርተር ዱቄት ተደርጓል። አገዛዙም የመድፉን ስብርባሪ በኬሻ አፍሶ ወስዷል።

በዚኸው ሰሞን አንድ ዙ23 በፋኖ ዶሽቃ ተመቶ ከጥቅም ውጭ ተደርጓል።

ብልፅግና በትምህርት ቤት ውስጥ የነበሩ ህፃናትን ጨፍጭፎ የሚኩራራባቸው እንዲሁም በንፁኋን መኖሪያ ቤት ላይ ጥቃት ፈፅሞ ህፃናት፣ አረጋውያንና ነፍሰጡር ሴቶችን ገድሎ “የፅንፈኛ ስብስብ ደመሰስኩ” በሚል የሚፎክርባቸው ዙ23ና መድፎችን፡ ፋኖ በሞርተርና ሌሎች ፀረ ከባድ መሣሪያዎችን ተጠቅሞ ልክ እንደ ጧፍ አንድዶ በደቂቃዎች ውስጥ ወደ አመድነት እየቀየራቸው መሆኑን የመረብ ሚዲያ የግንባር ዘጋቢዎች ለማረጋገጥ ችለዋል።

በተመሣሣይ፡ የሕወሓት ኃይሎች የብልፅግናን ሰው አልባ አውሮፕላን መትቶ የሚጥል የፀረ ድሮን ኃይል እያሰለጠኑ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህም በአገዛዙ ቤት ከባድ ድንጋጤን ቀስቅሷል