መብረቅ ክፍለ ጦር በምዕራብ ወሎ ግንባር ወግድ ወረዳ ውስጥ ፓራ ኮማንዶዎች እና የፓሊስ አባላት በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

መብረቅ ክፍለ ጦር በምዕራብ ወሎ ግንባር ወግድ ወረዳ ውስጥ ፓራ ኮማንዶዎች እና የፓሊስ አባላት በመደምሰስ ታላቅ ድል ተጎናፀፈ::

ትናንት ለዛሬ ታህሳስ 19/2018 ዓ.ም አጥቢያ የአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ንጉሥ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ከወግድ ከተማ 17 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ለሚ ተብላ በምትጠራው ታዳጊ ከተማ ውስጥ ካቢ የተባለ ስፍራ ላይ የፋሽስቱ አብይ አህመድ ወንበር ጠባቂዎች ክፉኛ የተመቱ ሲሆን 3 ፓሊሶች እና 10 ፓራ ኮማንዶዎች በድምሩ 13 የጠላት ኃይል አባላት ተደምስሰዋል::

ንስሮቹ በሰሩት በሌሊቱ ኦፕሬሽን ከ5 በላይ ፓራ ኮማንዶዎች ቁስለኛ ሲሆኑ 22 የሚሆኑት ደግሞ ወደ ሽነት ገደል ገብተዋል:: ገደል ከገቡት መካከል በርካቶች በህይወት መትረፍ እንዳልቻሉም ለማረጋገጥ ተችሏል::

የአየር ወለድ ኮማንዶ ዕዝ 105ኛ ክፍለ ጦር ኮማንዶዎች ለሚ የሚገኘውን ፓራ ኮማንዶ እና ፖሊስ ለማትረፍ ከወግድ ወረዳ ተንቀሳቅሰው የነበረ ቢሆንም መብረቆቹ መንገድን በእሳት ስላጠሩት ጠላት ምንም ማድረግ ሳይችል ቀርቷል::

ከመብረቅ ክፍለ ጦር ሰራዊት መካከል 1ኛ (አዳነ ሀብትነው) ሻለቃ እና ከ2ተኛ (ደምሰው ጎጡ) ሻለቃ የተውጣጡ አሃዶች ሌሊቱን የፈፀሙት የጦር ሜዳ ጀብዱን ተከትሎ ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ ስለገጠመው በቅጥረኝነት ከያዛቸው ተዋጊዎቹ መካከል ከሌሊቱ መዓት የተረፉት ተስፋ ቆርጠው በየ ገጠር ቀበሌዎች ተበትነዋል::
©አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ