ፋኖ በአምባሰል ግንባር በፈፀመው ስኬታማ የሞርተር ጥቃት አንድ የአገዛዙ መድፍ ሲወድም አራት ተኳሾች መገደላቸው ታውቋል።

ፋኖ በአምባሰል ግንባር በፈፀመው ስኬታማ የሞርተር ጥቃት አንድ የአገዛዙ መድፍ ሲወድም አራት ተኳሾች መገደላቸው ታውቋል።

አገዛዙ በአምባሰል ግንባር በታሪካዊቷ ውጫሌ ከተማ ዙሪያ ልዩ ቦታው ደንካ ሚካኤል ላይ መድፍ አጥምዶ የዘፈቀደ ድብደባ በመፈፀም የበርካታ ንፅኋንን ሕይወት ሲቀጥፍ፣ አያሌ ሀብት ንብረት ሲያወድም መቆየቱን መረብ ሚዲያ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገቡ አይዘነጋም።

ፋኖ ትናንት ታህሳስ 17/2018 ዓ/ም በፈፀመው ስኬታማ የሞርተር ጥቃት፡ ንፁኋንን ለእልቂት ሲዳርግ የነበረው የአገዛዙ መድፍ ከነ ተተኳሹ ዶግ አመድ ተደርጓል። በተጨማሪም አራት የመድፍ ተኳሾች በሞርተር ቅንቡላ ፍንጣሪ ተመተው ሕይወታቸው ማለፉን ምኒልክ ዕዝ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።

በምኒልክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር ስር በሞርተር ተኩስ ኢላማ “የሞርተር ቅምቡላን ከጥላት ኪስ ውስጥ መክተት ይችላሉ” የሚባልላቸው የ24ኛ ክ/ጦር ሜካናይዝድ ክፍል ምድብተኞች፡ በፈፀሙት ስኬታማ የሞርተር ጥቃት ነው የጠላት መድፍ ከነ ተተኳሹና ተኳሾቹ የወደመው።

በተያያዘ ዜና!

በዚኽው በአምባሰል ቀጠና ከታህሳስ 16/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተደረገ የጨበጣ ውጊያ በርካታ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸው ተሰምቷል።

መነሻቸውን ከውጫሌ ከተማና ከጎልቮ እንዲሁም ጭሳ አባዲማ ቀበሌዎች ያደረጉ ራሳቸውን “መከላከያ ሰራዊት” ብለው የሚጠሩ የፀረ አማራው አገዛዝ አገልጋዮች በሚኒሻና አድማ ብተና መሪነት በወረዳው አበት ቀበሌ ላይ ማጥቃት ከፍተው የነበረ ቢሆንም፡ ነገር ግን ከወደ ፋኖ የተሰነዘረባቸውን የፀረ ማጥቃት እርምጃን መቋቋም አቅቷቸው ከባድ የሆነ የሰብአዊና ቁሣዊ እንዲሁም ሞራላዊ ኪሳራ መከናነባቸውን መረብ ሚዲያ ለማረጋገጥ ችሏል።

በዚህ ውጊያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከነ መንገድ መሪዎቻቸው ሙትና ቁስለኛ የተደረጉ ሲሆን፡ አገዛዙ ከትናንት ምሽት ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት ድረስ ቁስለኞችን ለሕክምና ወደ ውጫሌና ሐይቅ ሲያጓጉዝ አድሯል።