እስራኤል ለሶማሊላንድ የሃገርነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሃገር ሆነች።
እስራኤል ዛሬ ለሶማሊላንድ የሃገርነት እውቅናን በይፋ ሰጥታለች።
ላለፉት 30 አመታት የሃገርነት እውቅና ለማግኘት ጥረት ላይ የነበረችው የነበረችው ሶማሊላንድ በመጨረሻም ሙከራዋ ተሳክቶ ከእስራኤል የሃገርነት እውቅና አግኝታለች።
የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እስራኤል እና ሶማሊላንድ የሙሉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ለመጀመር፣ አምባሳደሮችን ለመመደብና ኤምባሲዎችን ለመክፈት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁ ከሶማሊላንዱ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን እውቅናው ታሪካዊ ነው ብለውታል።
ኔታኔያሁ ዛሬ ሶማሊላንድን እንደ ነፃ እና ሉዓላዊ ሃገር እውቅና መስጠታቸውን አውጀዋል።
እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችው አመት ከፈጀ ንግግር በኋላ መሆኑንም አስታውቃለች።ላለፉት 30 አመታት የሃገርነት እውቅና ለማግኘት ጥረት ላይ የነበረችው የነበረችው ሶማሊላንድ በመጨረሻም ሙከራዋ ተሳክቶ ከእስራኤል የሃገርነት እውቅና አግኝታለች።
የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳር እስራኤል እና ሶማሊላንድ የሙሉ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ለመጀመር፣ አምባሳደሮችን ለመመደብና ኤምባሲዎችን ለመክፈት መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኔያሁ ከሶማሊላንዱ ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን እውቅናው ታሪካዊ ነው ብለውታል።
ኔታኔያሁ ዛሬ ሶማሊላንድን እንደ ነፃ እና ሉዓላዊ ሃገር እውቅና መስጠታቸውን አውጀዋል።
እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና የሰጠችው አመት ከፈጀ ንግግር በኋላ መሆኑንም አስታውቃለች።
እስራኤል እውቅናውን የሰጠችው በፕሬዚዳንት ትራምፕ አነሳሽነት በተረቀቀው የአብርሃም ስምምነት አማካኝነት መሆኑ ተገልጿል።
እነማን ተቃወሙ ?
ሶማሊያ ፦ የሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ሶማሊላንድ አንዷ የሶማሊያ አካል መሆኗን በመግለፅ የእስራኤልን ውሳኔ ተቃውማለች። የሀገሪቱ ግዛታዊ አንድነት እንዲከበር አሳስባለች።
ግብፅ ፦ ግብፅ ከሌሎች ጋር በመሆን እስራኤል የሰጠችውን እውቅና ተቃውማለች። የሶማሊያ አንድነት እና ሉዓላዊነት እንዲከበር አስገንዝባለች።
ቱርክ ፦ ቱርክ የእስራኤልን ውሳኔ ተቃውማለች።
ጅቡቲ ፦ ጅቡቲም የእስራኤልን ውሳኔ በመቃወም ከግብፅ ፣ ቱርክ እና ሶማሊያ ጋር በመሆን መግለጫ አውጥታለች።