በአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ 105ኛ ኮር 55ኛ ክ/ጦር ከዛሬ ታህሳስ 13/2018 ዓ/ም ጀምሮ ከባህር ዳር ጭንባ ቁንዝላ ደለጎ፣ ከዱርቤቴ ዝህብስት ወገዳ፣ ከዱርቤቴ ሀሙሲት ማማላ፣ ከዱርቤቴ ቀደምት ላሊበላ ልሁዲ ያለው አውራ ጎዳና ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆኖ እንደሚቆይ አስታውቋል።
ክፍለጦሩ በጠቀሳቸው ቀጠናዎች የአገዛዙን ተልዕኮ ተቀብለው ተሽከርካሪን በማገት ማውደምና አሽከርካሪን አግቶ ገንዘብ መጠየቅ፣ ተጓዦችን መዝረፍና መሰል እኩይ ተግባራትን በሚፈፅሙ ዘራፊ ባንዳዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ያመቸኝ ዘንድና በኦፕሬሽኑ ንፁኋኖች እንዳይጎዱብኝ በማሰብ ነው መንገዱ የሚዘጋው ሲል መግለፁን መረብ ሚዲያ ከክፍለጦሩ ሕዝብ ግንኙነት ክፍል ተመልክቷል።
በተጨማሪም ክፍለጦሩ፡ በተጠቀሱት ቀጠናዎች የተጣለውን እገዳ ተላልፎ የተገኘ አሽከርካሪም ይሁኑ ሌሎች ተጓዦች ለሚደርስባቸው ማንኛውም ችግር ኃላፊነቱን እራሳቸው ይወስዳሉ ሲል አሳስቧል።
ዘረፋ፣ እገታና መሰል እኩይ ተግባራትን በሚፈፅሙ ባንዳና ዘራፊዎች ላይ በአጭር ጊዜ ተገቢውን እርምጃ ወስጄ እስከማጠናቅቅ ሕዝቡ በትግስት ይጠብቀኝ ሲል ክፍለጦሩ በሕዝብ ግንኙነት ክፍሉ በኩል መልዕክት ማስተላለፉንም መረብ ሚዲያ ተመልክቷል።
ፋኖ፡ አገዛዙ የአማራ ሕዝብን በማሕበራዊና በኢኮንሚያዊ ሕይወቱ እረፍት እንዲነሱለት አደራጅቶ ያሰማራቸው ዘራፊ ወንበዴዎች ላይ ጥብቅ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።
በተመሣሣይ በሰሜን አማራ ቀጠና ከደብረ ታቦር ወረታ ያለው መስመርን የዘጋ በዘራፊዎች ላይ የተለየ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ጣቢያችን ከሰሞኑ መዘገቡ አይዘነጋም።