በሸገር ከተማ አስተዳደር ለመንግስት ቢሮ ማሰርያ ብር አምጡ እየተባሉ እንደሆነ ዜጎች ጠቁመዋል።
“በተጨማሪም ቤት ለቤት እየዞሩ የቴሌቪዥን ግብር ክፈሉ ይላሉ፣ የቴሌቪዥን ግብርን በተመለከተ EBC ከመብራት አገልግሎት ጋር ደረስኩት ባለው ስምምነት ላለፋት 3 ዓመታት መብራት ስንሞላ የቴሌቪዥን እየተቆረጠብን ነው የኖርነው፣ አሁን ሸገር ከተማ ከነቅጣቱ ክፈሉኝ እያለ ነው” ብለው ነዋሪዎቹ ያስረዳሉ።
አክለውም የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ከውሀና ፍሳሽ ጋር በመሆን ከነዋሪዎች የቆሻሻ ቢሰበስብም የወረዳ አስተዳደሩ የራሱን ማህበር አደራጅቶ በየወሩ ከነዋሪው በድጋሜ እንደሚያስከፍል ታውቋል። ( መሠረት ሚድያ )