አዳነች አቤቤ ቤታቸውን ያፈረሰችባቸውን ዜጎች ለፈረሰው ቤት ግብር ክፍሉ እያለች ነው

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ቤታቸው ፈርሶባቸው ወደሌላ ቦታ የተዛወሩ ሰዎችን በፈረሰው ቤት ስም የቤት ግብር እንዲከፍሉ የቴክስት መልዕክት እየላከላቸው እንደሆነ ታውቋል።

“ቤቴ ካዛንችስ ነበር፣ ቤቴም ሰፈሩም ከፈረሰ 3 ወራት አለፉ። ለፈረሰው ቤቴ ነው ግብር ክፈል የተባልኩት” ያሉት አንድ ግለሰብ “መሬት እና የቤት መስሪያ ወደፊት እንሰጣችኋለን ስላሉን የምንጠብቀው እሱን ነበር።

በአሁን ሰአት ከነቤተሰቤ  ቱሉ ዲምቱ ኮንዶሚንየም ተከራይተን እየኖርን ነው። ዛሬ ታድያ ላፈረሱት ቤቴ ግብር ክፈል ይሉኛል!” በማለት ተናግረዋል።